የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ነቅቶ ስለመጠበቅ ከኢየሱስ ሐዋርያት ተማሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
    • 4, 5. መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስንና የጉዞ ጓደኞቹን የመራቸው እንዴት ነው?

      4 ከሐዋርያቱ የምናገኘው የመጀመሪያው ትምህርት የሚከተለው ነው፦ የት መስበክ እንዳለባቸው የሚሰጣቸውን አመራር ለመከተል ንቁ ነበሩ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ያለ አንድ ዘገባ፣ ጳውሎስና የጉዞ ባልደረቦቹ ለየት ያለ ጉዞ ባደረጉበት ወቅት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተጠቅሞ እንዴት እንደመራቸው ይተርካል። (ሥራ 2:33) እስቲ ምን እንዳጋጠማቸው ለማወቅ አብረናቸው እንጓዝ።​—የሐዋርያት ሥራ 16:6-10⁠ን አንብብ።

  • ነቅቶ ስለመጠበቅ ከኢየሱስ ሐዋርያት ተማሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
    • 6, 7. (ሀ) ጳውሎስና ሌሎቹ መንገደኞች ወደ ቢቲኒያ ሲቃረቡ ምን አጋጠማቸው? (ለ) ደቀ መዛሙርቱ ምን ዓይነት ውሳኔ አደረጉ? ይህስ ምን ውጤት አስገኘ?

      6 ታዲያ እነዚህ ለመስበክ የጓጉ መንገደኞች ወዴት ሄዱ? ቁጥር 7 “ወደ ሚስያ በወረዱ ጊዜ ወደ ቢቲኒያ ሊገቡ ሞከሩ፤ ሆኖም የኢየሱስ መንፈስ አልፈቀደላቸውም” በማለት ይነግረናል። ጳውሎስና ባልደረቦቹ በእስያ እንዳይሰብኩ በመከልከላቸው ወደ ሰሜን በማቅናት በቢቲኒያ ከተሞች ለመስበክ አሰቡ። ይሁን እንጂ ወደ ቢቲኒያ ሲቃረቡ ኢየሱስ አሁንም በመንፈስ ቅዱስ ተጠቅሞ አገዳቸው። በዚህ ጊዜ እነዚህ ወንድሞች ግራ ሳይገባቸው አልቀረም። ምን እንደሚሰብኩና እንዴት እንደሚሰብኩ ያውቃሉ፤ የት እንደሚሰብኩ ግን አያውቁም። ሁኔታውን በዚህ መልክ ልናስቀምጠው እንችላለን፦ ወደ እስያ የሚያስገባቸውን በር አንኳኩ፤ ሆኖም በሩ ሳይከፈትላቸው ቀረ። ወደ ቢቲኒያ የሚያስገባውን በር አንኳኩ፤ አሁንም በሩ አልተከፈተላቸውም። ታዲያ ማንኳኳታቸውን ያቆሙ ይሆን? በፍጹም፣ እነዚህ ቀናተኛ ሰባኪዎች ማንኳኳታቸውን አላቆሙም!

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ