-
ነቅቶ ስለመጠበቅ ከኢየሱስ ሐዋርያት ተማሩመጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
-
-
4, 5. መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስንና የጉዞ ጓደኞቹን የመራቸው እንዴት ነው?
4 ከሐዋርያቱ የምናገኘው የመጀመሪያው ትምህርት የሚከተለው ነው፦ የት መስበክ እንዳለባቸው የሚሰጣቸውን አመራር ለመከተል ንቁ ነበሩ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ያለ አንድ ዘገባ፣ ጳውሎስና የጉዞ ባልደረቦቹ ለየት ያለ ጉዞ ባደረጉበት ወቅት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተጠቅሞ እንዴት እንደመራቸው ይተርካል። (ሥራ 2:33) እስቲ ምን እንዳጋጠማቸው ለማወቅ አብረናቸው እንጓዝ።—የሐዋርያት ሥራ 16:6-10ን አንብብ።
-
-
ነቅቶ ስለመጠበቅ ከኢየሱስ ሐዋርያት ተማሩመጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
-
-
7 በዚህ ጊዜ እነዚህ ወንድሞች ያደረጉት ውሳኔ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ይመስላል። ቁጥር 8 “ስለዚህ በሚስያ አልፈው ወደ ጥሮአስ ወረዱ” በማለት የወሰዱትን እርምጃ ይነግረናል። ሰዎቹ ወደ ምዕራብ ዘወር በማለት በርካታ ከተሞችን እያለፉ 563 ኪሎ ሜትር በእግራቸው ከተጓዙ በኋላ ወደ መቄዶንያ የሚወስደውን መርከብ ለመያዝ ይበልጥ አመቺ ወደሆነችው የጥሮአስ ወደብ ደረሱ። በዚያም ጳውሎስና ባልንጀሮቹ ለሦስተኛ ጊዜ በሩን አንኳኳ። በዚህ ጊዜ ግን በሩ ወለል ብሎ ተከፈተላቸው! ቁጥር 9 ቀጥሎ የሆነውን ሲተርክ “ጳውሎስም ሌሊት በራእይ አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ ‘ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን’ ብሎ ሲለምነው አየ” ይላል። በመጨረሻ ጳውሎስ የት መስበክ እንዳለበት አወቀ። መንገደኞቹ ምንም ጊዜ ሳያባክኑ ወደ መቄዶንያ የሚወስዳቸው መርከብ ላይ ተሳፈሩ።
-