የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ልድያ እንግዳ ተቀባይ የነበረችው የአምላክ አገልጋይ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መስከረም 15
    • “የቀይ ሐር ሻጭ”

      ልድያ የመቄዶንያ ዋና ከተማ በሆነችው በፊልጵስዩስ ትኖር ነበር። ይሁን እንጂ ትውድ አገሯ ልድያ የተባለ ክፍለ ሃገር ከተማ በሆነችውና በትንሿ እስያ ምዕራባዊ ክፍል በምትገኘው በትያጥሮን ነበር። በዚህም ምክንያት አንዳንዶች “ልድያ” የሚለው ስም ፊልጵስዩስ ከመጣች በኋላ የተሰጣት የቅጽል ስም ነው በማለት ይናገራሉ። በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠከረላት ሴት “ሳምራዊት ሴት” ተብላ ልትጠራ እንደምትችል ሁሉ እርሷም “ልድያዊት” ተብላ ትጠራ ነበር። (ዮሐንስ 4:9) ልድያ “ቀይ ሐር” ወይም ቀይ ቀለም የተነከሩ ጌጣጌጦችን ትሸጥ ነበር። (ሥራ 16:12, 14) በትያጥሮንና በፊልጵስዩስ ቀለም የሚነክሩ ሰዎች ይኖሩ እንደነበር የከርሰ ምድር ጥናት ተመራማሪዎች በቁፋሮ ባገኟቸው የተቀረጹ ጽሑፎች ተረጋግጧል። ልድያ ወደ ፊልጵስዩስ የመጣችው በሥራዋ ምክንያት ማለትም የራሷን ንግድ ለማካሄድ አሊያም በትያጥሮን የሚገኙ ቀለም ነካሪዎችን ወክላ ለመሥራት ሊሆን ይችላል።

      ቀይ ሐር ከተለያዩ ነገሮች ሊገኝ ይችላል። በጣም ውድ የሆነው ሐር የሚገኘው በባሕር ውስጥ ከሚኖሩ አንዳንድ የቀንድ አውጣ ዝርያዎች ነው። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይኖር የነበረ ማርሻል የተባለ አንድ ሮማዊ ባለ ቅኔ በጢሮስ (ቀይ ሐር የሚመረትበት ሌላው ቦታ ነው) የሚገኘው ከሁሉ የተሻለው ቀይ ሐር አንድ የቀን ሠራተኛ 2,500 ቀናት ሠርቶ የሚያገኘውን ደሞዝ የሚያክል 10,000 የሮማ ሳንቲም ወይም 2,500 ዲናሬ ሊያወጣ እንደሚችል ተናግሯል። ከእንዲህ ዓይነቱ ቀይ ሐር የሚሠሩ ልብሶች ጥቂት ሰዎች ብቻ ሊያገኟቸው የሚችሉ የቅንጦት ልብሶች እንደሆኑ ግልጽ ነው። በዚህም ምክንያት ልድያ በኑሮዋ የበለጸገች ልትሆን ትችላለች። ኑሮዋ ምንም ይሁን ምን ሐዋርያው ጳውሎስንና የእርሱ የሥራ ባልደረቦች የነበሩትን ሉቃስን፣ ሲላስን፣ ጢሞቴዎስንና ሌሎች ሰዎችን በእንግድነት መቀበል ችላ ነበር።

  • ልድያ እንግዳ ተቀባይ የነበረችው የአምላክ አገልጋይ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መስከረም 15
    • “እግዚአብሔርን የምታመልክ”

      ልድያ “እግዚአብሔርን የምታመልክ” ነበረች። ምናልባት ወደ አይሁድ እምነት የተለወጠችው ሃይማኖታዊ እውነትን ፈልጋ ሳይሆን አይቀርም። ልድያ ጥሩ ሥራ የነበራት ቢሆንም ቁሳዊ ሀብት የማሳደድ ምኞት ግን አልነበራትም። ከዚህ ይልቅ ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ጊዜ ትመድብ ነበር። “ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት፤” በዚህም የተነሳ እውነትን ተቀበለች። እንዲያውም ‘እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ተጠመቀች።’—ሥራ 16:14, 15

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ