የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 12/1 ገጽ 11
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሩሳሌም “የታላቁ ንጉሥ ከተማ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • የአርኪኦሎጂ ማስረጃ ለክርስቲያኖች እምነት የግድ አስፈላጊ ነውን?
    ንቁ!—2002
  • ምድራዊቱ ኢየሩሳሌም ከሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም ጋር ስትነጻጸር
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
  • የክርስትና እምነት በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩት አይሁዶች ተዳረሰ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 12/1 ገጽ 11

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በ33 ዓ.ም. በጴንጤቆስጤ ዕለት በእርግጥ አይሁዳውያን “በምድር ዙሪያ ካለ አገር ሁሉ” መጥተው ነበር?

በ33 የጴንጤቆስጤ ዕለት ኢየሩሳሌም ውስጥ በሕዝብ በተጨናነቀ ጎዳና ላይ ሰዎች ተሰብስበው እያወሩ

በ33 ዓ.ም. በጴንጤቆስጤ ዕለት ኢየሩሳሌም ውስጥ በሕዝብ የተጨናነቀ ጎዳና

በሐዋርያት ሥራ 2:5-11 ላይ ከምናገኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ በተጨማሪ የዘመኑ ታሪክ ጸሐፊ የነበረው ፋይሎ በ33 ዓ.ም. በጴንጤቆስጤ ዕለት ወደ ኢየሩሳሌም ስለጎረፈው ሕዝብ ጽፏል።

ፋይሎ ወደ ኢየሩሳሌም ስለመጡት ሰዎች እንዲህ ብሏል፦ “በዓሉ በደረሰ ቁጥር እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ ከበርካታ ከተሞች ይጎርፉ የነበረ ሲሆን አንዳንዶቹ በየብስ፣ ሌሎቹ ደግሞ በባሕር ተጉዘው ከምሥራቅ፣ ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ ይመጡ ነበር።” በተጨማሪም ፋይሎ የታላቁ ሄሮድስ የልጅ ልጅ የነበረው ቀዳማዊ አግሪጳ፣ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ለካሊጉላ ከላከው ደብዳቤ ላይ የጠቀሰው ሐሳብ አለ። በዚያ ደብዳቤ ላይ አግሪጳ ኢየሩሳሌምን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦ “ቅድስቲቱ ከተማ . . . ለይሁዳ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች በርካታ አገሮችም ዋና ከተማ ናት፤ ይህም ሊሆን የቻለው በየጊዜው ወደ አጎራባች አገሮች እየሄዱ በዚያ የሰፈሩ ማኅበረሰቦች ስላሉ ነው።”

አግሪጳ በጠቀሳቸው ቦታዎች ላይ የአይሁዳውያን ማኅበረሰቦች ተቋቁመው የነበረ ሲሆን እንደ ሜሶጶጣሚያ፣ ሰሜን አፍሪካ፣ ትንሿ እስያ፣ ግሪክ እንዲሁም የሜድትራንያን ደሴቶች ባሉ ርቀው የሚገኙ ቦታዎች ይኖሩ ነበር። ዮአኪም ዬሬሚያስ የተባሉ ምሁር እንዲህ ብለዋል፦ “ምንም እንኳ በዝርዝሩ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም ስለተደረገ ጉዞ የተጠቀሰ ነገር ባይኖርም አንድ ጎልማሳ የሆነ አይሁዳዊ ወደዚያ የመሄድ ግዴታ ስላለበት አይሁዳውያን ወደ ከተማዋ ተጉዘው እንደሚሆን ግልጽ ነው።”—ዘዳግም 16:16

በኢየሩሳሌም ለሚከበረው የአይሁዳውያን በዓል የሚመጡ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ማረፊያ የሚያገኙት እንዴት ነበር?

በኢየሩሳሌም የተገኘ የመታጠቢያ ገንዳ ፍርስራሽ

በኢየሩሳሌም የተገኘ የመታጠቢያ ገንዳ ፍርስራሽ

በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመታዊ በዓላት ይከበሩ የነበረ ሲሆን እነሱም ፋሲካ፣ ጴንጤቆስጤና የዳስ በዓል ነበሩ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመላው እስራኤልና አይሁዳውያን ከሚኖሩባቸው አገሮች ሁሉ ለዚህ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር። (ሉቃስ 2:41, 42፤ የሐዋርያት ሥራ 2:1, 5-11) እነዚህ ሁሉ መንገደኞች የሚያርፉበት ቦታ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል።

አንዳንዶች ወዳጆቻቸው ጋር ሲያርፉ ሌሎች ደግሞ በትንንሽ ሆቴሎችና በማረፊያ ቦታዎች ያድሩ ነበር። ብዙ ሰዎች በከተማዋ ውስጥ ወይም በከተማው ግንብ ዙሪያ ድንኳን ተክለው ይሰፍሩ ነበር። ኢየሱስ በኢየሩሳሌም በቆየበት በመጨረሻው ቀን ቅርብ በሆነችው በቢታንያ አርፏል።—ማቴዎስ 21:17

በቤተ መቅደሱ አቅራቢያ በርካታ የመታጠቢያ ገንዳዎችን የያዙ ብዙ ቤቶች ተገኝተዋል። እነዚህ ቤቶች መንገደኞቹ የሚያድሩባቸውና ወደ ቤተ መቅደሱ ከመግባታቸው በፊት የሚታጠቡባቸው የማረፊያ ቦታዎች እንደሆኑ ይታሰባል። ከእነዚህ ቤቶች በአንዱ ላይ ቲኦደተስ የተባሉ ካህንና የአካባቢው የምኩራብ አለቃ “ቶራ (የሕጉ መጻሕፍት) የሚነበብበት ምኩራብ እንደገነቡ . . . ከዚህ በተጨማሪ ችግረኛ የሆኑ እንግዶች የሚያርፉበት ቤትና የተለያዩ ክፍሎችን እንደሠሩ እንዲሁም ውኃ እንዲገባ እንዳደረጉ” የሚናገር ጽሑፍ ሰፍሯል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ