የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በተሰሎንቄ ለምሥራቹ መታገል
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሰኔ 1
    • ጳውሎስ ወደ አንድ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሄድ በአብዛኛው ቀድሞ የሚያናግረው አይሁዳውያንን ነበር፤ ይህን የሚያደርገውም አይሁዳውያን ስለ ቅዱሳን ጽሑፎች ያላቸው እውቀት ውይይት ለመጀመር መንገድ ስለሚከፍትና ምሥራቹን ለመረዳት ስለሚያቀልላቸው ነው። አንድ ምሁር እንደገለጹት ይህ የጳውሎስ ልማድ ለአገሩ ሰዎች ያለውን አሳቢነት የሚጠቁም አሊያም ደግሞ አይሁዳውያንንና ፈሪሃ አምላክ ያላቸውን ሌሎች ሰዎች “እንደ መሸጋገሪያ በመጠቀም ለአሕዛብ [ለመስበክ]” ጥረት እንደሚያደርግ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።​—የሐዋርያት ሥራ 17:2-4

      በመሆኑም ጳውሎስ፣ ተሰሎንቄ ሲደርስ መጀመሪያ ወደ ምኩራብ በመግባት “ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ [ከአይሁዳውያን] ጋር ተወያየ፤ ክርስቶስ መከራ መቀበሉና ከሞት መነሳቱ የግድ አስፈላጊ እንደነበር ማስረጃ እየጠቀሰ በማብራራትና በማስረዳት ‘ይህ እኔ እያሳወቅኳችሁ ያለሁት ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ ነው’ አላቸው።”​—የሐዋርያት ሥራ 17:2, 3, 10

      ጳውሎስ ስለ መሲሑ ማንነትና ስለሚጫወተው ሚና የተናገረው ሐሳብ አወዛጋቢ ነበር። እሱ የገለጸው መከራ የተቀበለና የተገደለ መሲሕ፣ አይሁዳውያን ከሚጠብቁት ድል አድራጊና ጦረኛ መሲሕ ፈጽሞ የተለየ ነበር። ጳውሎስ አይሁዳውያንን ለማሳመን ሲል ከእነሱ ጋር ‘ይወያይ፣’ ‘ማስረጃ እየጠቀሰ ያብራራ’ እንዲሁም ‘ያስረዳ’ ነበር፤ እነዚህ አንድ ውጤታማ አስተማሪ ተለይቶ የሚታወቅባቸው ዘዴዎች ናቸው።a ይሁን እንጂ ጳውሎስ እነዚህን አስደናቂ ትምህርቶች ሲያካፍላቸው አድማጮቹ ምን ምላሽ ሰጡ?

  • በተሰሎንቄ ለምሥራቹ መታገል
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሰኔ 1
    • a ጳውሎስ፣ አሁን በ⁠መዝሙር 22:7፤ 69:21፤ ኢሳይያስ 50:6፤ 53:2-7፤ ዳንኤል 9:26 ላይ የሚገኙትን ጥቅሶች እንደ ማስረጃ አቅርቦ ሊሆን ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ