-
የአምላክን ቃል አንብቡ በእውነትም አገልግሉትመጠበቂያ ግንብ—1996 | ግንቦት 15
-
-
5. የአምላክን እውነት ለማግኘት ምን ነገር ያስፈልገናል?
5 የአምላክ እውነት በዋጋ ሊተመን የማይችል ውድ ሀብት ነው። ይህን እውነት ማግኘት የሚቻለው በመቆፈር ማለትም ሳይታክቱ ቅዱሳን ጽሑፎችን በመመርመር ነው። ጥበብ ማግኘትና ለይሖዋ አክብሮታዊ ፍርሃት ማሳየት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት የምንችለው ልክ በልጅነት ዕድሜ ላይ እንደሚገኙ ተማሪዎች ልባችንን ክፍት አድርገን ከታላቁ አስተማሪ ስንማር ብቻ ነው። (ምሳሌ 1:7፤ ኢሳይያስ 30:20, 21) እርግጥ ነው የተማርነውን ነገር ከቅዱሳን ጽሑፎች ማረጋገጥ ይኖርብናል። (1 ጴጥሮስ 2:1, 2) በቤርያ ይኖሩ የነበሩት አይሁዳውያን “በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና፦ ነገሩ [ጳውሎስ የተናገረው ነገር] እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።” የቤርያ ሰዎች ይህን ማድረጋቸው አስመሰገናቸው እንጂ አላስኮነናቸውም።—ሥራ 17:10, 11
-
-
የአምላክን ቃል አንብቡ በእውነትም አገልግሉትመጠበቂያ ግንብ—1996 | ግንቦት 15
-
-
7. ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለንን ማስተዋል ለማሳደግ ምን ያስፈልጋል? ለምንስ?
7 ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለን ማስተዋል እንዲያድግ ከአምላክ መንፈስ ወይም አንቀሳቃሽ ኃይል የሚገኘው መመሪያ ያስፈልገናል። ‘መንፈስ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን በመመርመር’ ትርጉማቸውን ግልጽ ያደርግልናል። (1 ቆሮንቶስ 2:10) በተሰሎንቄ የነበሩት ክርስቲያኖች የሰሟቸውን ትንቢቶች ‘ሁሉ መፈተን’ ነበረባቸው። (1 ተሰሎንቄ 5:20, 21) ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች ሲጽፍ (በ50 እዘአ ገደማ) ከግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች መካከል በወቅቱ ተጽፎ የነበረው የማቴዎስ ወንጌል ብቻ ነበር። በመሆኑም በተሰሎንቄና በቤርያ የነበሩት ሰዎች ሁሉን መፈተን ይችሉ የነበረው የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎችን የግሪክ ሴፕቱጀንት ትርጉም በመመርመር ነበር ማለት ነው። እነርሱ ቅዱሳን ጽሑፎችን ማንበብና ማጥናት አስፈልጓቸው እንደነበር ሁሉ እኛም እንዲሁ ማድረግ ይኖርብናል።
-