የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 5
  • ዘዴኛነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዘዴኛነት
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጳውሎስ ምን አድርጓል?
  • ከጳውሎስ ምን እንማራለን?
  • ጳውሎስን ምሰል
  • “አምላክን እንዲፈልጉትና . . . እንዲያገኙት”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • ትሕትና
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • መስኩን የምትመለከቱት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • “ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት ማድረግህን ቀጥል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 5

ውይይት መጀመር

ሐዋርያው ጳውሎስ የአቴንስ ሰዎችን ሲያስረዳ።

ሥራ 17:22, 23

ምዕራፍ 5

ዘዴኛነት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ንግግራችሁ ምንጊዜም . . . ለዛ ያለው ይሁን።”—ቆላ. 4:6

ጳውሎስ ምን አድርጓል?

ሐዋርያው ጳውሎስ የአቴንስ ሰዎችን ሲያስረዳ።

ቪዲዮ፦ ጳውሎስ ለአቴንስ ሰዎች ሰበከ

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም የሐዋርያት ሥራ 17:22, 23ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ጳውሎስ በአቴንስ ከተማ ያለውን የሐሰት አምልኮ ሲያይ ምን ተሰማው?—የሐዋርያት ሥራ 17:16ን ተመልከት።

  2. ለ. የአቴንስ ሰዎችን ከማውገዝ ይልቅ የሚያምኑበትን ነገር መሠረት በማድረግ ምሥራቹን በዘዴ የሰበከላቸው እንዴት ነው?

ከጳውሎስ ምን እንማራለን?

2. ምን እንደምንናገር እንዲሁም እንዴትና መቼ እንደምንናገር በጥንቃቄ ማሰባችን ሰሚ ጆሮ ለማግኘት ይረዳናል።

ጳውሎስን ምሰል

3. የምትጠቀምባቸውን ቃላት በጥንቃቄ ምረጥ። ለምሳሌ የክርስትናን እምነት የማይከተል ሰው ስታነጋግር፣ መጽሐፍ ቅዱስን በምታስተዋውቅበት ወይም ኢየሱስን በምትጠራበት መንገድ ላይ ለውጥ ማድረግ ሊያስፈልግህ ይችላል።

4. ለማረም አትቸኩል። ሐሳቡን በነፃነት እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ጋር የሚጋጭ ነገር ቢያነሳ እንኳ ‘ትክክል አይደለህም’ ለማለት አትቸኩል። (ያዕ. 1:19) አዳምጠው፤ አመለካከቱን መረዳት የምትችለው እንዲህ ካደረግክ ነው።—ምሳሌ 20:5

5. የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ሐሳቡን ተጋራ እንዲሁም አመስግነው። ግለሰቡ ሃይማኖቱ ትክክል እንደሆነ ከልቡ ያምን ይሆናል። በቅድሚያ በሚያስማሟችሁ ነገሮች ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው፤ ከዚያም ቀስ በቀስ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት እንዲገነዘብ እርዳው።

ተጨማሪ ጥቅሶች

ምሳሌ 25:15፤ 2 ጢሞ. 2:23-26፤ 1 ጴጥ. 3:15

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ