-
“አምላክን እንዲፈልጉትና . . . እንዲያገኙት”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
13. ጳውሎስ ጽንፈ ዓለም የተገኘበትን መንገድ በተመለከተ ምን ብሏል? ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክትስ ምንድን ነው?
13 አምላክ ጽንፈ ዓለምን ፈጥሯል። ጳውሎስ “ዓለምንና በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረው አምላክ፣ እሱ የሰማይና የምድር ጌታ ስለሆነ በእጅ በተሠሩ ቤተ መቅደሶች ውስጥ አይኖርም” ሲል ተናግሯል።d (ሥራ 17:24) ጽንፈ ዓለም የተገኘው እንዲሁ በአጋጣሚ አይደለም። ሁሉንም ነገር የፈጠረው እውነተኛው አምላክ ነው። (መዝ. 146:6) አቴናም ሆነች ሌሎች ጣዖታት ክብራቸው የተመካው ሰዎች በሚሠሩላቸው ቤተ መቅደሶችና መሠዊያዎች ላይ ነው፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠረው ሉዓላዊ ጌታ ግን በሰው እጅ በተሠራ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሊኖር አይችልም። (1 ነገ. 8:27) ጳውሎስ ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት ግልጽ ነው፦ እውነተኛው አምላክ፣ ሰዎች በሠሯቸው ቤተ መቅደሶች ውስጥ ከሚገኙት ሰው ሠራሽ ጣዖታት እጅግ የላቀ ነው።—ኢሳ. 40:18-26
-
-
“አምላክን እንዲፈልጉትና . . . እንዲያገኙት”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
d “ዓለም” ተብሎ የተተረጎመው ግሪክኛ ቃል ኮስሞስ ሲሆን ግሪካውያን ይህን ቃል ግዑዙን ጽንፈ ዓለም ለማመልከት ይጠቀሙበት ነበር። ጳውሎስም ከግሪካውያን አድማጮቹ ጋር ሊያግባባው በሚችል መንገድ ለመናገር ጥረት እያደረገ ስለነበር ይህን ቃል የተጠቀመበት ከዚህ አገባቡ አንጻር ሊሆን ይችላል።
-