የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አጵሎስ አንደበተ ርቱዕ የሆነ የክርስትና እውነት ሰባኪ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | ጥቅምት 1
    • “ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረ”

      በ52 እዘአ ገደማ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ሉቃስ እንደሚተርክልን “የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የተባለ አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረና ጥሩ የአነጋገር ችሎታ ያለው ሰው ነበረ። ስለ ጌታ መንገድ የተማረና በመንፈስም የተቃጠለ ሆኖ ስለ ኢየሱስ በትክክል ይሰብክና ያስተምር ነበር። ይሁን እንጂ እርሱ የሚያውቀው የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ ነበር። እርሱ በድፍረት በምኩራብ መናገር ጀመረ።”—ሥራ 18:24-26 የ1980 ትርጉም

      የግብጽዋ እስክንድርያ ከሮም ቀጥላ በዓለም ሁለተኛዋ ሰፊ ከተማ ስትሆን በዘመኑ ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን በጣም ትልቅ ደረጃ ካላቸው የባሕል ማዕከሎች አንዷ ነበረች። አጵሎስ ስለ ዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች የነበረውን ጥልቅ እውቀትና ጥሩ የንግግር ችሎታ ያገኘው በዚህች ከተማ ከሚኖረው በርካታ የአይሁድ ማኅበረሰብ ካገኘው ትምህርት ሳይሆን አይቀርም። አጵሎስ ስለ ኢየሱስ ያወቀው የት እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመናገር ያስቸግራል። ኤፍ ኤፍ ብሩስ የተባሉ ምሁር እንደሚሉት “ከአገር ወደ አገር የሚዘዋወርና ምናልባትም ተዘዋዋሪ ነጋዴ ስለነበረ ከተጓዘባቸው ቦታዎች በአንዱ ክርስቲያን ሰባኪዎችን ሊያገኝ ይችል ነበር።” ያም ሆነ ይህ ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር የነበረ ቢሆንም “የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ” ያውቅ ስለነበር በ33 እዘአ ከዋለው የጰንጠቆስጤ ቀን በፊት የተመሠከረለት ይመስላል።

      ዮሐንስ መጥምቁ የኢየሱስ መንገድ ጠራጊ እንደመሆኑ መጠን ለመላው የእስራኤል ብሔር ጠንካራ ምስክርነት የሰጠ ሲሆን ብዙዎችም ንስሐ ለመግባታቸው ምልክት እንዲሆን በእጁ ተጠምቀዋል። (ማርቆስ 1:5፤ ሉቃስ 3:15, 16) በርካታ ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት በሮማ ግዛት ይኖሩ የነበሩ አይሁዳውያን ስለ ኢየሱስ የነበራቸው እውቀት በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻዎች ከተሰበከላቸው አላለፈም ነበር። ደብልዩ ጄ ኮኒቢር እና ጄ ኤስ ሃውሰን እንዳሉት “ክርስትናቸው ጌታችን አገልግሎት በጀመረበት ወቅት ከነበረው እልፍ አላለም። የክርስቶስ ሞት ስላለው ሙሉ ትርጉም ደንቆሮዎች ነበሩ። እንዲያው ከሙታን ስለመነሳቱ እንኳን ያወቁ አይመስልም።” አጵሎስም መንፈስ ቅዱስ በ33 እዘአ በዋለው የጰንጠቆስጤ ቀን ስለመፍሰሱ ያወቀ አይመስልም። ይሁን እንጂ ስለ ኢየሱስ መጠነኛ የሆነ ትክክለኛ እውቀት አግኝቶ ስለነበረ ይህንን ያገኘውን እውቀት ለራሱ ብቻ ይዞ ለመኖር አልፈለገም። እንዲያውም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለሚያውቀው ነገር በድፍረት ይናገር ነበር። ይሁን እንጂ ቅንዓቱና ግለቱ ገና በትክክለኛ እውቀት ላይ አልተመሠረተም ነበር።

  • አጵሎስ አንደበተ ርቱዕ የሆነ የክርስትና እውነት ሰባኪ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | ጥቅምት 1
    • የሉቃስ ትረካ በመቀጠል “ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፣ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት” ይላል። (ሥራ 18:26) አቂላና ጵርስቅላ የአጵሎስ እምነት ከእነርሱ እምነት ጋር የሚመሳሰልባቸው ብዙ መንገዶች እንዳሉ ቢገነዘቡም ያልተሟላ እውቀቱን በሕዝብ ፊት ለማረም አልሞከሩም። አጵሎስን ለመርዳት ብዙ ጊዜ በግል አነጋግረውት እንደነበረ ልንገምት እንችላለን። ታዲያ ይህ “ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረው” አጵሎስ የተሰጠውን እርዳታ እንዴት ተቀበለው? (ሥራ 18:24 የ1980 ትርጉም) አጵሎስ አቂላንና ጵርስቅላን ከማግኘቱ በፊት የነበረውን ያልተሟላ መልእክት ለሕዝብ ሲሰብክ ቆይቶ እንደነበረ መገመት አያዳግትም። ኩሩ ሰው ቢሆን ኖሮ ምንም ዓይነት እርማት ለመቀበል እምቢተኛ ይሆን ነበር። እርሱ ግን እውቀቱን የተሟላ እንዲያደርግ የቀረበለትን እርዳታ በትህትናና በአመስጋኝነት ተቀበለ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ