-
አጵሎስ አንደበተ ርቱዕ የሆነ የክርስትና እውነት ሰባኪመጠበቂያ ግንብ—1996 | ጥቅምት 1
-
-
አጵሎስ በአገልግሎቱ ያገኘው የመጀመሪያ ውጤት በጣም ግሩም ነበር። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ “በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር፤ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና” ይላል።—ሥራ 18:27, 28
አጵሎስ በዝግጅቱና በቅንዓቱ ወንድሞችን እያበረታታ ራሱን ለጉባኤ አገልግሎት ሰጥቶ ነበር። የተሳካ ውጤት ያገኘበት ቁልፍ ምን ነበር? አጵሎስ የተፈጥሮ ችሎታ ያለው ከመሆኑም በላይ ከአይሁዳውያን ጋር በድፍረት ለመከራከር ችሏል። ከዚህ በላይ ግን ከቅዱሳን ጽሑፎች ምክንያቱን ያስረዳ ነበር።
-