የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መጥምቁ ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • የዮሐንስ መልእክት የአድማጮቹን ስሜት የሚቀሰቅስ ነው። ብዙዎቹ ንስሐ መግባት ማለትም አስተሳሰባቸውንና አካሄዳቸውን በመለወጥ የቀድሞ ሕይወታቸውን እርግፍ አድርገው መተው እንዳለባቸው ተገነዘቡ። “በኢየሩሳሌምና በመላዋ ይሁዳ እንዲሁም በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ክልል ሁሉ የሚኖሩ ሰዎች” ወደ ዮሐንስ እየመጡ ነው። (ማቴዎስ 3:5) ወደ ዮሐንስ ከመጡት ሰዎች ብዙዎቹ ንስሐ ገብተዋል። እሱም በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ እያጠለቀ አጠመቃቸው። ይህን ያደረገው ለምንድን ነው?

      ንስሐ የገቡ አይሁዳውያን ለመጠመቅ ወደ ዮሐንስ ሲመጡ

      የዮሐንስ ጥምቀት፣ ሰዎቹ የአምላክን የቃል ኪዳን ሕግ በመተላለፍ ለፈጸሙት ኃጢአት ከልብ ንስሐ መግባታቸውን የሚያሳይ ምልክት ወይም ማረጋገጫ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 19:4) ለመጠመቅ ብቁ የሆኑት ግን ሁሉም አይደሉም። የሃይማኖት መሪዎች የሆኑ አንዳንድ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እሱ ሲመጡ ዮሐንስ “የእፉኝት ልጆች” በማለት አውግዟቸዋል። አክሎም እንዲህ አላቸው፦ “ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ። ‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ ብላችሁ አታስቡ። አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ሊያስነሳለት እንደሚችል ልነግራችሁ እወዳለሁ። መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።”—ማቴዎስ 3:7-10

  • መጥምቁ ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • በእርግጥም ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ስለቀረበ ንስሐ ግቡ” ብሎ መናገሩ ተገቢ ነው። (ማቴዎስ 3:2) የዮሐንስ መልእክት፣ ይሖዋ የሾመው ንጉሡ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎቱን ሊጀምር መሆኑን ለሕዝቡ የሚጠቁም ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ