-
ኢየሱስ ምን ባሕርያት አሉት?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
6. ኢየሱስ ለጋስ ነው
ኢየሱስ ብዙ ገንዘብ ባይኖረውም ለሌሎች በልግስና ይሰጥ ነበር፤ እኛንም ለጋስ እንድንሆን አበረታቶናል። የሐዋርያት ሥራ 20:35ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ኢየሱስ በተናገረው መሠረት ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?
ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ብዙ ገንዘብ ባይኖረንም እንኳ ለሌሎች መስጠት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥራና ስለ ገንዘብ ምን ይላል?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
3. ገንዘባችንን ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ ለጋስ አምላክ ነው፤ እኛም “ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ” በመሆን የእሱን ምሳሌ እንከተላለን። (1 ጢሞቴዎስ 6:18) ጉባኤውን በመደገፍ እንዲሁም የተቸገሩ ሰዎችን በተለይ መንፈሳዊ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በመርዳት ገንዘባችንን ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ ልንጠቀምበት እንችላለን። ይሖዋ ትኩረት የሚያደርገው በምንሰጠው የገንዘብ መጠን ላይ ሳይሆን ለመስጠት በተነሳሳንበት ምክንያት ላይ ነው። ከልባችን በልግስና ስንሰጥ ደስተኞች እንሆናለን፤ ይሖዋንም እናስደስታለን።—የሐዋርያት ሥራ 20:35ን አንብብ።
-