-
“ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ!”መጠበቂያ ግንብ—2001 | ታኅሣሥ 15
-
-
በቁጣ ገንፍሎ የወጣው ሕዝብ ራሱን መከላከል የሚችልበት መንገድ የሌለውን አንድ ሰው መደብደብ ጀመረ። የሕዝቡ አቋም ሰውዬው ሞት ይገባዋል የሚል ነው። አለቀለት፣ አይተርፍም በሚባልበት ሰዓት ላይ ወታደሮች ደርሰው ሰውዬውን እንደምንም ብለው በቁጣ ካበደው ሕዝብ አስጣሉት። ሰውዬው ሐዋርያው ጳውሎስ ሲሆን ደብዳቢዎቹ የጳውሎስን ስብከት አምርረው የሚቃወሙና ቤተ መቅደስ አርክሷል ብለው የሚከሱት አይሁዳውያን ናቸው። ከሞት ያዳኑት ሰዎች ደግሞ ቀላውዴዎስ ሉስዮስ በሚባል አዛዥ የሚመሩ ሮማውያን ናቸው። ጳውሎስ በግርግሩ መካከል በወንጀለኝነት ተጠርጥሮ ተያዘ።
የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጨረሻዎቹ ሰባት ምዕራፎች ጳውሎስ ከተያዘበት ጊዜ አንስቶ ስለተከሰቱት ሁኔታዎች ይተርካሉ። ጳውሎስ ሕግ ፊት ቀርቦ ስላሳለፈው ታሪክ፣ በእርሱ ላይ ስለተመሠረተው ክስ፣ እሱ ስላቀረበው የመከላከያ ሐሳብ እንዲሁም ስለ ሮማውያን የፍርድ አሰጣጥ ሂደት የተወሰነ እውቀት ማግኘታችን እነዚህን ምዕራፎች ጥሩ አድርገን መረዳት እንችል ዘንድ ተጨማሪ ብርሃን ይፈነጥቅልናል።
-
-
“ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ!”መጠበቂያ ግንብ—2001 | ታኅሣሥ 15
-
-
የቀላውዴዎስ ሉስዮስ ኃላፊነት በኢየሩሳሌም ውስጥ ጸጥታ ማስጠበቅንም ይጨምራል። የእርሱ የበላይ የነበረው ሮማዊው የይሁዳ አገረ ገዥ በቂሣርያ ይኖር ነበር። ሉስዮስ በጳውሎስ ላይ የወሰደው እርምጃ አንድ ግለሰብ ሊደርስበት ከሚችለው አደጋ ለመጠበቅ ወይም ሁከት ፈጣሪውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተደረገ እርምጃ እንደሆነ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል። የአይሁዳውያን ሁከት እየተባባሰ በሄደ ጊዜ ሉስዮስ እስረኛውን በአንቶኒያ ግንብ ወደሚገኘው ጦር ሠፈር እንዲወስደው አስገደደው።—ሥራ 21:27–22:24
-