የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 17 በዚህ ጊዜ በቦታው ከቆሙት መካከል አንዳንዶቹ ደነገጡ! የደነገጡት ግን ጳውሎስ በመመታቱ ሳይሆን በሰጠው መልስ ነበር። “የአምላክን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህ?” አሉት። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ፣ የሰጠው መልስ በትሕትናና ለሕጉ አክብሮት በማሳየት ረገድ ጥሩ ትምህርት የሚሆናቸው ነው። “ወንድሞች፣ እኔ እኮ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅኩም። ምክንያቱም ‘በሕዝብህ ገዢ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ ተብሎ ተጽፏል” አላቸው።d (ሥራ 23:4, 5፤ ዘፀ. 22:28) አሁን ጳውሎስ ለየት ያለ ዘዴ ተጠቀመ። የሳንሄድሪን አባላት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን መሆናቸውን ስላወቀ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ እኔ ከፈሪሳውያን የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ። ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ ተስፋ በማመኔ ነው።”—ሥራ 23:6

  • “የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • d አንዳንዶች እንደሚሉት ከሆነ ጳውሎስ ሊቀ ካህናቱን ያላወቀው አጥርቶ የማየት ችግር ስለነበረበት ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ ለረጅም ጊዜ በኢየሩሳሌም ስላልነበረ በወቅቱ ያለው ሊቀ ካህናት ማን እንደሆነ አላወቀ ይሆናል። አሊያም ብዙ ሰው ስለነበር እንዲመታ ትእዛዝ የሰጠው ማን እንደሆነ መለየት ስላቃተው ሊሆን ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ