-
ይቅርታ መጠየቅ—እርቅ ለመፍጠር የሚያስችል ቁልፍመጠበቂያ ግንብ—2002 | ኅዳር 1
-
-
መቼ ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባ የሚያውቀው ሌላው ምሳሌ ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። በአንድ ወቅት ሳንሄድሪን በተባለው የአይሁዳውያን ፍርድ ቤት ቀርቦ ለቀረበበት ክስ የመከላከያ ሐሳብ ማቅረብ ነበረበት። ጳውሎስ በሐቀኝነት በተናገራቸው ቃላት የተናደደው ሊቀ ካህናት ሐናንያ አፉን ይመቱት ዘንድ አጠገቡ የቆሙትን አዘዘ። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ፣ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?” አለው። ሁኔታውን ይከታተሉ የነበሩ ሰዎች ሊቀ ካህናቱን ተሳድበሃል በማለት ሲወቅሱት ሐዋርያው ጳውሎስ “ወንድሞች ሆይ፣ ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር ተብሎ ተጽፎአልና” በማለት ስህተቱን ያላንዳች ማንገራገር አምኗል።—ሥራ 23:1-5
ጳውሎስ ፈራጅ ሆኖ የተሾመ ሰው ሕገ ወጥ ድርጊት መፈጸም የለበትም ብሎ መናገሩ ትክክል ነበር። ያም ሆኖ ለሊቀ ካህናቱ አክብሮት እንደሌለው በሚያስመስል መንገድ በመናገሩ ይቅርታ ጠይቋል።a ጳውሎስ ይቅርታ መጠየቁ ሸንጎው ሐሳቡን እንዲሰማ በር ከፍቷል። ጳውሎስ የሸንጎው አባላት እርስ በርስ የማይግባቡበትን ነጥብ ያውቅ ስለነበር በትንሣኤ ተስፋ በማመኑ የተነሳ ፍርድ ፊት መቅረቡን ተናገረ። በዚህ ምክንያት በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ከፍተኛ ጠብ ተነሳ። ፈሪሳውያኑም ከጳውሎስ ጎን ቆሙ።—ሥራ 23:6-10
-
-
ይቅርታ መጠየቅ—እርቅ ለመፍጠር የሚያስችል ቁልፍመጠበቂያ ግንብ—2002 | ኅዳር 1
-
-
a ጳውሎስ ሊቀ ካህናቱን መለየት ያልቻለው በነበረበት አጥርቶ የማየት ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል።
-