-
“ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ!”መጠበቂያ ግንብ—2001 | ታኅሣሥ 15
-
-
ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ የአይሁድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ጳውሎስን ‘በአይሁዳውያን መካከል ሁከት የሚያስነሳ በሽታ’ ሆኗል በማለት በፊልክስ ፊት ከሰውታል። በተጨማሪም “የናዝራውያን ወገን” ቀንደኛ መሪ ነው እንዲሁም ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሞክሯል በማለት ከሰሱት።—ሥራ 24:1-6

አይሁዳውያን ጳውሎስ የሚያስተምረው የአይሁድን እምነት ወይም ሕጋዊ እውቅና ያገኘን ሃይማኖት (ሪሊጂዮ ሊኪታ) አይደለም የሚል አመለካከት ነበራቸው። ይልቁንም ሕገ ወጥ እንዲያውም ዓመፅን የሚያነሳሳ ትምህርት ተደርጎ መታየት አለበት ይላሉ።
በተጨማሪም ጳውሎስ “በሽታ ሆኖ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት” አስነስቷል ብለውታል። (ሥራ 24:5) ንጉሥ ቀላውዴዎስ በዚያው ወቅት አካባቢ በእስክንድርያ የሚኖሩ አይሁዳውያንን “በመላው ዓለም ወረርሽኝ አስፋፍተዋል” በማለት አውግዟቸው ነበር። የወቀሳው መመሳሰል የሚያስደንቅ ነው። አድሪያን ኤን ሼርዊን ዊት የተባሉ አንድ ታሪክ ጸሐፊ እንዲህ ብለዋል:- “ይህ ክስ በንጉሥ ቀላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት ወይም በኔሮ አስተዳደር የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ በአንድ አይሁዳዊ ላይ ተቃውሞ ለማነሳሳት የተሰነዘረ ነበር። አይሁዳውያን አገረ ገዥው የጳውሎስ ስብከት በሮም ግዛት ሥር በሚገኙ የአይሁድ ማኅበረሰቦች ውስጥ ብጥብጥ የሚፈጥር ነው ብለው ለማሳመን እየሞከሩ ነበር። አገረ ገዥዎቹ ሃይማኖታዊ በሆነ ጉዳይ ውስጥ እጃቸውን እንደማያስገቡ ስለገባቸው ጉዳዩን ወደ ፖለቲካ ለመጠምዘዝ እየሞከሩ ነበር።”
-