የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 9/15 ገጽ 8-9
  • ጴጥሮስ በጰንጠቆስጤ ዕለት ሰበከ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጴጥሮስ በጰንጠቆስጤ ዕለት ሰበከ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ሰማ
  • እኛ የምናገኘው ትምህርት
  • “በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • ‘የመንግሥተ ሰማያት ቁልፎች’ ምንድን ናቸው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ይቅር ባይነትን ከጌታው ተምሯል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ፈተናዎች ቢደርሱበትም ታማኝ መሆኑን አሳይቷል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 9/15 ገጽ 8-9

የይሖዋን ፈቃድ ፈጽመዋል

ጴጥሮስ በጰንጠቆስጤ ዕለት ሰበከ

ጊዜው 33 እዘአ የፀደይ ወራት ሲሆን የጠዋቱ አየር ደስ የሚል ነበር። ሰው ሁሉ ፍንድቅድቅ ብሏል! ወዲያና ወዲህ ሽር ጉድ የሚሉ አይሁዳውያንና ወደ አይሁድ እምነት የተለወጡ ሰዎች የኢየሩሳሌምን ጎዳናዎች አጨናንቀዋል። እንደ ኤላም፣ ሜሶጶጣሚያ፣ ቀጰዶቅያ እንዲሁም ግብጽና ሮም ከመሳሰሉት ቦታዎች የተሰባሰቡ ሰዎች ናቸው። የየአካባቢያቸውን ልብስ ለብሰው ማየትና የተለያዩ ቋንቋዎቻቸውን ሲናገሩ መስማት እንዴት የሚያስደስት ነበር! አንዳንዶቹ በዚህ ልዩ በዓል ላይ ለመገኘት ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው መጥተዋል። ይህ ልዩ በዓል ምንድን ነው? ጰንጠቆስጤ ማለትም የገብስ መከር ከተሰበሰበ በኋላ የሚከበር የአይሁዳውያን አስደሳች ክብረ በዓል ነው።—ዘሌዋውያን 23:15-21

በቤተ መቅደሱ መሠዊያ ላይ የቀረበው መሥዋዕት ጢስ እየተትጎለጎለ ይወጣል፤ ሌዋውያኑም የሃሌልን መዝሙሮች ያዜማሉ። (መዝሙር 113 እስከ 118) ልክ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ገደማ አንድ አስገራሚ ነገር ተፈጸመ። ከሰማይ “እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ” ያለ ድምፅ መጣ። 120 የሚሆኑት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውበት የነበረውን ቤት ሞላው። የቅዱስ ጽሑፉ ዘገባ እንዲህ ይላል፦ “እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፣ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።”—ሥራ 2:1-4

እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ሰማ

ወዲያውም ብዙ ደቀ መዛሙርት ከቤት ውስጥ ግልብጥ ብለው ወጡ። በጣም የሚያስገርም ነው! በተሰበሰበው ሕዝብ የተለያየ ቋንቋ መናገር ይችሉ ነበር። ከፋርስ የመጣውም ጎብኚ ሆነ የግብጽ ተወላጅ የሆነው ሰው የገሊላ ሰዎች በእነርሱ ቋንቋ ሲናገሩ ሲሰሙ ምን ያህል እንደሚገረሙ እስቲ አስበው! የተሰበሰበው ሕዝብ በመገረም ስሜት ተውጦ እንደነበር ምንም አያጠራጥርም። “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” ሲሉ ጠይቀዋል። አንዳንዶችም “ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል” እያሉ በደቀ መዛሙርቱ ማፌዝ ጀመሩ።—ሥራ 2:12, 13

ከዚያም ሐዋርያው ጴጥሮስ ተነሥቶ ለተሰበሰበው ሕዝብ ተናገረ። ይህ ተአምራዊ በልሳን የመናገር ስጦታ አምላክ በነቢዩ በኢዩኤል በኩል “በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ” ሲል የገባው ቃል ፍጻሜ መሆኑን አብራራ። (ሥራ 2:14-21፤ ኢዩኤል 2:28-32) አዎን፣ አምላክ በኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ላይ መንፈስ ቅዱስ ማፍሰሱ ነበር። ይህም ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ በሰማይ በአምላክ ቀኝ እንዳለ የሚያሳይ ግልጽ ማስረጃ ነበር። “እንግዲህ” አለ ጴጥሮስ “ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።”—ሥራ 2:22-36

አድማጮቹ ምን ምላሽ ሰጡ? ዘገባው እንደሚለው “ልባቸው ተነካ፣ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት፦ ወንድሞች ሆይ፣ ምን እናድርግ? አሉአቸው።” ጴጥሮስም መልሶ ‘ንስሐ ግቡ እያንዳንዳችሁም ተጠመቁ’ አላቸው። 3,000 የሚያክሉት እንደተነገራቸው አደረጉ! ከዚህ በኋላ “በሐዋርያትም ትምህርት . . . ይተጉ ነበር።”—ሥራ 2:37-42

ጴጥሮስ በዚህ ታላቅ በዓል ላይ ቀዳሚ ሆኖ በመናገር ኢየሱስ እንደሚሰጠው ቃል ከገባለት ‘የመንግሥተ ሰማያት ቁልፎች’ መካከል የመጀመሪያውን ተጠቅሞበታል። (ማቴዎስ 16:19) እነዚህ ቁልፎች የተለያዩ ሕዝቦች ልዩ መብት እንዲያገኙ በር ከፍተዋል። ይህ የመጀመሪያ ቁልፍ አይሁዳውያን በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። ቆይቶም ሁለተኛው ቁልፍ ሳምራውያን ሦስተኛው ቁልፍ ደግሞ አሕዛብ ተመሳሳይ አጋጣሚ እንዲያገኙ አስችለዋል።—ሥራ 8:14-17፤ 10:44-48

እኛ የምናገኘው ትምህርት

እነዚህ አይሁዳውያንና ወደ አይሁድ እምነት የተለወጡ ሰዎች በአምላክ ልጅ መገደል በኅብረተሰብ ደረጃ ተጠያቂ ቢሆኑም እንኳ ጴጥሮስ “ወንድሞች” በማለት በአክብሮት ጠርቷቸዋል። (ሥራ 2:29) ዓላማው ንስሐ እንዲገቡ ማነሳሳት እንጂ እነርሱን መኮነን አልነበረም። በመሆኑም አቀራረቡ ገንቢ ነበር። እውነታውን ቁልጭ አድርጎ በማስቀመጥ በቅዱሳን ጽሑፎች ማስረጃ አስደግፎ አቅርቧል።

ዛሬም ምሥራቹን የሚሰብኩ ሁሉ የጴጥሮስን ምሳሌ መኮረጃቸው የተገባ ነው። ከአድማጮቻቸው ጋር የጋራ መሠረት በመጣል ከቅዱሳን ጽሑፎች በጥበብ ለማስረዳት መጣር ይኖርባቸዋል። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ገንቢ በሆነ መልኩ ካቀረብነው ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ጥሩ ምላሽ ይሰጣሉ።—ሥራ 13:48

ጴጥሮስ በጰንጠቆስጤ ዕለት ያሳየው ቅንዓትና ልበ ሙሉነት ከሰባት ሳምንታት ገደማ በፊት ኢየሱስን ከካደበት ሁኔታ ፈጽሞ የተለየ ነው። በዚያ ወቅት ጴጥሮስ የሰው ፍርሃት አሽመድምዶት ነበር። (ማቴዎስ 26:69-75) ይሁን እንጂ ኢየሱስ ስለ ጴጥሮስ ምልጃ አቅርቧል። (ሉቃስ 22:31, 32) ኢየሱስ ከትንሣኤው በኋላ ለጴጥሮስ መታየቱ ይህን ሐዋርያ እንዳበረታው እሙን ነው። (1 ቆሮንቶስ 15:5) ከዚህም የተነሣ የጴጥሮስ እምነት አልጠፋም። ፈጣን ለውጥ በማድረግ በድፍረት መስበኩን ተያያዘው። በጰንጠቆስጤ ዕለት ብቻ ሳይሆን ከዚያ በኋላ ባለው የሕይወቱ ዘመን ሁሉ በድፍረት መስበኩን ቀጥሏል።

እኛስ አንድ ዓይነት ምናልባትም እንደ ጴጥሮስ ያለ ስህተት ብንሠራስ? ንስሐ እንግባ፣ ይቅርታ እንዲደረግልን እንጸልይ ከዚያም መንፈሳዊ እርዳታ ለማግኘት እንነሣ። (ያዕቆብ 5:14-16) ከዚያ በኋላ የምናቀርበው ቅዱስ አገልግሎት በመሐሪው ሰማያዊ አባታችን በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንደሚያገኝ እርግጠኞች ሆነን ወደ ፊት መግፋት እንችላለን።—ዘጸአት 34:6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ