የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ!”
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ታኅሣሥ 15
    • ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ የአይሁድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ጳውሎስን ‘በአይሁዳውያን መካከል ሁከት የሚያስነሳ በሽታ’ ሆኗል በማለት በፊልክስ ፊት ከሰውታል። በተጨማሪም “የናዝራውያን ወገን” ቀንደኛ መሪ ነው እንዲሁም ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሞክሯል በማለት ከሰሱት።​—⁠ሥራ 24:​1-6

      መጀመሪያ ላይ ጳውሎስን የደበደቡት ሰዎች ጥሮፊሞስ የተባለውን አሕዛብ ለአይሁዳውያን ብቻ ወደተፈቀደው አደባባይ ያስገባው መስሏቸው ነበር።a (ሥራ 21:​28, 29) እንደ እውነቱ ከሆነ ሕግ ተላልፏል መባል የነበረበት ጥሮፊሞስ ነው። ሆኖም አይሁዳውያኑ ጳውሎስ አድርጎታል ብለው ያሰቡትን ነገር ሕግ ተላላፊውን እንደ መርዳት ወይም እንደ ማደፋፈር አድርገው ቆጥረውት ከሆነ እሱም ቢሆን ሞት የሚገባው ጥፋት ተገኝቶበታል ሊባል ይችል ነበር። ይህ ጥፋት ለሞት የሚያበቃ ወንጀል ነው የሚለውን ጉዳይ ሮምም እውቅና ሰጥታው የነበረ ይመስላል። ስለሆነም ጳውሎስ በሉስዮስ ሳይሆን በአይሁድ ቤተ መቅደስ ጠባቂዎች ተይዞ ቢሆን ኖሮ ሳንሄድሪን ያለ ምንም ችግር ጉዳዩን አይቶ ብይን ሊሰጠው ይችል ነበር።

  • “ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ!”
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ታኅሣሥ 15
    • a የአሕዛብን አደባባይ ከውስጠኛ አደባባይ የሚለይ ሦስት ክንድ ከፍታ ያለው አንድ የግንብ አጥር ይገኛል። በዚህ ግድግዳ ላይ አንዳንዱ በግሪክኛ ሌላው ደግሞ በላቲንኛ የሚከተለው ማስጠንቀቂያ ተጽፎበታል:- “ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ይህን ግድግዳ ወይም በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለውን አጥር አልፎ መግባት አይኖርበትም። ገብቶ የተገኘ ማንኛውም ሰው ለሚከተለው የሞት ቅጣት ተጠያቂው ራሱ ነው።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ