የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ!”
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ታኅሣሥ 15
    • ጳውሎስ የመከላከያ መልሱን አንድ በአንድ አቀረበ። ‘ምንም ዓይነት ሁከት አልፈጠርኩም። እርግጥ ነው እነርሱ “ኑፋቄ” ብለው ከሚጠሩት ወገን ነኝ። ሆኖም ይህ ራሱ የሚያሳየው የአይሁድን ሕግ የምከተል መሆኔን ነው። ረብሻውን የቀሰቀሱት አንዳንድ የእስያ አይሁዶች ናቸው። ክስ ካላቸው እዚህ መጥተው አቤቱታቸውን ማቅረብ ነበረባቸው።’ ጳውሎስ ጉዳዩ በአይሁዳውያን መካከል የተፈጠረ ሃይማኖታዊ አለመግባባት እንደሆነ አድርጎ አቅርቦታል። ሮማውያን ደግሞ ይህን ዓይነቱን ጉዳይ ለመዳኘት እምብዛም ብቃት አልነበራቸውም። ፊልክስ በቋፍ ላይ የሚገኙትን አይሁዳውያንን ይበልጥ እንዳያበሳጫቸው በመስጋት ጉዳዩን በእንጥልጥል ተወው። ጳውሎስ ጉዳዩን ማየት ያለብን እኛ ነን ለሚሉት አይሁዳውያን አልፎ አልተሰጠም ወይም በሮማውያን ሕግ መሠረት አልተዳኘም ወይም ደግሞ በነጻ አልተሰናበተም። ፊልክስ ያኔውኑ ውሳኔ እንዲሰጥ የሚያስገድደው ምክንያት ያልነበረ ከመሆኑ ሌላ አይሁዳውያኑን ደስ ለማሰኘት ሲልና ጳውሎስ ጉቦ እንዲሰጠው ተስፋ በማድረግ ጉዳዩን ለሌላ ጊዜ አስተላልፎታል።​—⁠ሥራ 24:​10-19, 26b

  • “ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ!”
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | ታኅሣሥ 15
    • b እንዲህ ማድረግ በእውነቱ ሕገ ወጥ ነበር። አንድ ምንጭ እንደሚከተለው ይላል:- “እጅ መንሻን አስመልክቶ በወጣው ሕግ ማለትም በሌክስ ሬፒቱነደሩም ላይ እንደተገለጸው አንድ ባለ ሥልጣን ወይም አስተዳዳሪ አንድን ሰው ለማሰርም ሆነ ለመፍታት፣ ብይን ለመስጠትም ሆነ ላለመስጠት ወይም አንድን እስረኛ በነጻ ለማሰናበት ጉቦ መጠየቅም ሆነ መቀበል ፈጽሞ የተከለከለ ነው።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ