-
“ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
5. ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ የያዘው እንዴት ነበር?
5 ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ፊስጦስ በቂሳርያ ‘በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ።’b ጳውሎስና ከሳሾቹ ፊቱ ቆመዋል። ጳውሎስ ለቀረበበት መሠረተ ቢስ ክስ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “እኔ በአይሁዳውያን ሕግ ላይም ሆነ በቤተ መቅደሱ ወይም በቄሳር ላይ ምንም የፈጸምኩት በደል የለም።” ሐዋርያው ንጹሕ ሰው በመሆኑ በነፃ መለቀቅ ይገባዋል። ፊስጦስ ምን ውሳኔ ያስተላልፍ ይሆን? በአይሁዳውያን ዘንድ መወደድ ስለፈለገ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ እኔ ባለሁበት መዳኘት ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀው። (ሥራ 25:6-9) እንዴት ያለ ፌዝ ነው! ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሰ ከሳሾቹ ሊዳኙት ነው፤ ይህ ከሆነ ደግሞ እንደሚገደል የታወቀ ነው። በዚህ ወቅት ፊስጦስ የፍትሕ ነገር ያሳሰበው አይመስልም፤ ለፖለቲካው የሚጠቅመውን ነገር ማድረግ የፈለገ ይመስላል። ከዓመታት በፊት፣ አገረ ገዢው ጳንጥዮስ ጲላጦስም ተመሳሳይ ፍርደ ገምድልነት ታይቶበታል፤ ያኔ ግን ይህን ግፍ የሠራው ከጳውሎስ በላይ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው እስረኛ ላይ ነበር። (ዮሐ. 19:12-16) በዛሬው ጊዜ ያሉ ዳኞችም በፖለቲካዊ ጫና ሊሸነፉ ይችላሉ። በመሆኑም ፍርድ ቤቶች የአምላክን ሕዝቦች የሚመለከቱ ጉዳዮችን በሚያዩበት ጊዜ ማስረጃዎችን ያላገናዘበ ውሳኔ ቢያስተላልፉ መገረም አይኖርብንም።
-
-
“ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
b እዚህ ላይ የተጠቀሰው ‘የፍርድ ወንበር’ መድረክ ላይ የሚቀመጥ ወንበር ነው። ወንበሩ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ መቀመጡ ዳኛው ለሚያስተላልፈው ውሳኔ ክብደት ይጨምራል፤ ውሳኔው የማያዳግም ተደርጎ እንዲታይም ያደርጋል። ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ የቀረቡትን ክሶች የተመለከተው በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር።
-