የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር አሳይቷል
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሰኔ 15
    • 7, 8. ሁለት ፍጹማን ሰዎች የተከተሉት አካሄድ የተለያየ ውጤት ያስገኘው እንዴት ነው?

      7 ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ፣ የሰው ልጆች ከወረሱት ኃጢአት ነፃ መውጣት የሚችሉበትን ዝግጅት አድርጓል። ጳውሎስ ይህ ሊሆን የቻለው ከጊዜ በኋላ በመጣ ሌላ ፍጹም ሰው አማካኝነት እንደሆነ ገልጿል፤ ይህ ሰው ሁለተኛው አዳም ነው ሊባል ይችላል። (1 ቆሮ. 15:45) ይሁን እንጂ እነዚህ ሁለት ፍጹም ሰዎች የተከተሉት አካሄድ በጣም የተለያየ ውጤት አስከትሏል። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?—ሮም 5:15, 16⁠ን አንብብ።

      8 ጳውሎስ “ስጦታው ያስገኘው ነገር በደሉ ካስከተለው ነገር የተለየ ነው” በማለት ጽፏል። አዳም በደለኛ ስለነበር በእሱ ላይ የሞት ፍርድ መበየኑ ተገቢ ነበር፤ በመሆኑም አዳም ሞቷል። ይሁንና የሚሞተው እሱ ብቻ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ “በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ሞተዋል” ይላል። በአዳም ላይ ሞት እንዲበየን ያደረገው የአምላክ ፍትሕ እኛን ጨምሮ ፍጽምና በጎደላቸው ዘሮቹ ሁሉ ላይ ተመሳሳይ ፍርድ እንዲበየን የግድ ይላል። ያም ሆኖ ፍጹም ሰው የሆነው ኢየሱስ ከዚህ የተለየ ውጤት ማስገኘት እንደሚችል ማወቃችን የሚያጽናና ነው። ኢየሱስ የሚያስገኘው ውጤት ምንድን ነው? ጳውሎስ “ሁሉም ዓይነት ሰዎች ጻድቃን ተብለው በመጠራት ለሕይወት እንዲበቁ ያስችላል” በማለት መልሱን ሰጥቶናል።—ሮም 5:18

      9. በ⁠ሮም 5:16, 18 ላይ የሚገኘው “ጻድቃን ተብለው እንዲጠሩ” የሚለው አገላለጽ ምን ትርጉም አለው?

      9 “ጻድቃን ተብለው እንዲጠሩ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ አገላለጽ ምን ትርጉም አለው? አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ ይህን አገላለጽ በተመለከተ እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦ “ተለዋጭ ዘይቤን በመጠቀም ሁኔታው ከሕግ አንጻር ተገልጿል ማለት ይቻላል። አንድ ሰው በአምላክ ፊት ያለው ሁኔታ እንደተለወጠ የሚጠቁም ሐሳብ ነው፤ ይሁን እንጂ ግለሰቡ ውስጣዊ ለውጥ ይኖረዋል ማለት አይደለም። . . . ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር አምላክን እንደ ዳኛ አድርጎ ይገልጸዋል፤ ይህ ዳኛ፣ ጻድቅ ባለመሆኑ ምክንያት ተከስሶ በምሳሌያዊ አነጋገር በእሱ ችሎት ፊት ለቀረበው ሰው ፈርዶለታል። አምላክ፣ ተከሳሹ ነፃ እንደሆነ የሚገልጽ ብያኔ አስተላልፏል።”

  • አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር አሳይቷል
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ሰኔ 15
    • 14, 15. አምላክ ጻድቃን ብሎ የጠራቸው ሰዎች ምን ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል? ያም ሆኖ ምን ማድረግ ያስፈልጋቸዋል?

      14 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ አንድ ሰው የወረሰውን ኃጢአትም ሆነ በሕይወቱ ውስጥ የፈጸማቸውን ስህተቶች ይቅር ማለቱ ምን ያህል ታላቅ ስጦታ እንደሆነ እስቲ አስበው! ሰዎች ክርስቲያን ከመሆናቸው በፊት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም፤ ሆኖም አምላክ በቤዛው መሠረት ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር ማለት ይችላል። ጳውሎስ “የብዙዎችን በደል ተከትሎ የመጣው ስጦታ . . . ብዙዎች ጻድቃን ተብለው እንዲጠሩ አስችሏል” ሲል ጽፏል። (ሮም 5:16) ፍቅር የተንጸባረቀበትን ይህን ስጦታ (ይኸውም ጻድቃን ተብለው መጠራትን) የተቀበሉት ሐዋርያትና ሌሎች ሰዎች እውነተኛውን አምላክ በእምነት ማምለካቸውን መቀጠል አለባቸው። ይህን ማድረጋቸው ወደፊት ምን ሽልማት ያስገኝላቸዋል? “የአምላክን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅን ነፃ ስጦታ [የሚቀበሉት] በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ሕይወት አግኝተው ነገሥታት ሆነው [ይገዛሉ]።” በእርግጥም የጽድቅ ስጦታ የሚያስገኘው ውጤት የተለየ ነው። ይህ ስጦታ ሕይወት ያስገኛል።—ሮም 5:17፤ ሉቃስ 22:28-30⁠ን አንብብ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ