-
እውነት ሲኦል አለ? የመጽሐፍ ቅዱሱ ሲኦል ምንድን ነው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
አምላክ በደነገገው መሠረት የኃጢአት ቅጣት፣ ሞት እንጂ ሲኦል ውስጥ በእሳት መቃጠል አይደለም። አምላክ ለመጀመሪያው ሰው ለአዳም የነገረው የአምላክን ሕግ ቢጥስ በሞት እንደሚቀጣ ነው። (ዘፍጥረት 2:17) በሲኦል ለዘላለም እንደሚሠቃይ አልነገረውም። አዳም ኃጢአት ከሠራ በኋላ ደግሞ አምላክ ቅጣቱ ምን እንደሆነ ሲነግረው “አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ” ብሎታል። (ዘፍጥረት 3:19) ከመኖር ወደ አለመኖር ይሄዳል ማለት ነው። የአምላክ ሐሳብ አዳምን ሲኦል እሳት ውስጥ መክተት ቢሆን ኖሮ ይህን ይነግረው እንደነበረ ምንም ጥያቄ የለውም። አምላክ ሕጎቹን መጣስ የሚያስከትለውን ቅጣት አልቀየረውም። አዳም ኃጢአት ከሠራ ከብዙ ዓመታት በኋላ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ በአምላክ መንፈስ መሪነት “የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው” ሲል ጽፏል። (ሮም 6:23) ከዚህ ተጨማሪ ቅጣት የሚጣልበት ምክንያት የለም፤ ምክንያቱም “የሞተ ከኃጢአቱ ነፃ ወጥቷል።”—ሮም 6:7
-