የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕይወትንና ሰላምን እንድታገኙ እንደ መንፈስ ፈቃድ ተመላለሱ
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ኅዳር 15
    • 8 በውስጡ ብዙ ትእዛዛትን ያቀፈው የሙሴ ሕግ ኃጢአተኞችን ይኮንናል። ከዚህም በተጨማሪ በሕጉ ሥር የሚያገለግሉት የእስራኤል ሊቀ ካህናት ፍጹማን ያልነበሩ ሲሆን የሚያቀርቡት መሥዋዕትም ኃጢአትን ለማስወገድ አይችልም ነበር። በመሆኑም “ሕጉ ከሥጋ ባሕርይ የተነሳ ደካማ” ሊሆን ችሏል። ይሁንና አምላክ “የገዛ ራሱን ልጅ በኃጢአተኛ ሥጋ አምሳል በመላክ” እና ቤዛ እንዲሆን በማድረግ “የሥጋን ኃጢአት ኮንኗል”፤ ይህም ሕጉ “ሊፈጽመው ያልቻለውን ነገር” ለማከናወን አስችሏል። በዚህም የተነሳ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ ባላቸው እምነት መሠረት ጻድቃን ተብለው ለመጠራት ችለዋል። እነዚህ ክርስቲያኖች “እንደ ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ መንፈስ ፈቃድ” እንዲመላለሱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል። (ሮም 8:3, 4⁠ን አንብብ።) በእርግጥም “የሕይወትን አክሊል” ማግኘት ከፈለጉ ምድራዊ ሕይወታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ ይህን ማሳሰቢያ በታማኝነት መከተል ይኖርባቸዋል።​—ራእይ 2:10

  • ሕይወትንና ሰላምን እንድታገኙ እንደ መንፈስ ፈቃድ ተመላለሱ
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ኅዳር 15
    • 10. ለኃጢአትና ለሞት ሕግ የተገዛነው እንዴት ነው?

      10 ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።” (ሮም 5:12) ሁላችንም የአዳም ዘር እንደመሆናችን መጠን ለኃጢአትና ለሞት ሕግ ተገዝተናል። በመሆኑም ኃጢአተኛው ሥጋችን አምላክን የሚያሳዝኑ ነገሮችን እንድናደርግ ሁልጊዜ ይገፋፋናል፤ እነዚህ ነገሮች ደግሞ የሚመሩት ወደ ሞት ነው። ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ያሉትን ድርጊቶችና ባሕርያት “የሥጋ ሥራዎች” ሲል ጠርቷቸዋል። አክሎም “እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽሙ የአምላክን መንግሥት አይወርሱም” ብሏል። (ገላ. 5:19-21) በሌላ አባባል እነዚህ ሰዎች እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚመላለሱ ናቸው። (ሮም 8:4) ‘ማንኛውንም ነገር ለማድረግ የሚያንቀሳቅሳቸው’ እና ‘ሕይወታቸውን የሚመሩበት’ መመሪያ ሙሉ በሙሉ ሥጋዊ ነው። ለመሆኑ እንደ ሥጋ ፈቃድ እየተመላለሱ እንደሆኑ ተደርገው የሚቆጠሩት ዝሙት የሚፈጽሙ፣ ጣዖት የሚያመልኩ፣ በመናፍስታዊ ድርጊት የሚካፈሉ ወይም እነዚህን የመሳሰሉ ከባድ ኃጢአቶችን የሚሠሩ ሰዎች ብቻ ናቸው? አይደለም፣ አንዳንዶች ተራ የባሕርይ ችግር አድርገው የሚመለከቷቸው እንደ ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣ የከረረ ጭቅጭቅና ምቀኝነት የመሳሰሉ ባሕርያትም ከሥጋ ሥራዎች የሚፈረጁ ናቸው። ታዲያ እንደ ሥጋ ፈቃድ ከመመላለስ ራሴን ሙሉ በሙሉ ነፃ አውጥቻለሁ ብሎ መናገር የሚችል ሰው ይኖራል?

  • ሕይወትንና ሰላምን እንድታገኙ እንደ መንፈስ ፈቃድ ተመላለሱ
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ኅዳር 15
    • 12 ያለንበት ሁኔታ ከከባድ በሽታ ለመዳን ከሚደረግ ጥረት ጋር ይመሳሰላል። አንድ ሰው ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ለመዳን ከፈለገ ሐኪሙ የሚያዘውን ማድረግ ይኖርበታል። በቤዛው ላይ እምነት እንዳለን በተግባር ማሳየታችን ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ ሊያወጣን ቢችልም ዛሬም ጭምር ፍጽምና የጎደለንና ኃጢአተኞች ነን። ጥሩ መንፈሳዊ ጤንነት እንዲኖረን እንዲሁም የአምላክን ሞገስና በረከት እንድናገኝ ከዚህ የበለጠ ነገር ያስፈልገናል። ጳውሎስ ‘የሕጉን የጽድቅ መሥፈርት’ ለመፈጸም እንደ መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚኖርብንም ጠቅሷል።

      እንደ መንፈስ ፈቃድ መመላለስ የሚቻለው እንዴት ነው?

      13. እንደ መንፈስ ፈቃድ መመላለስ ሲባል ምን ማለት ነው?

      13 ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረው ‘መመላለስ’ ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል አንድ ቦታ ወይም ግብ ላይ ለመድረስ መገስገስን ያመለክታል። በመሆኑም እንደ መንፈስ ፈቃድ ለመመላለስ ከፈለግን የማያቋርጥ መንፈሳዊ እድገት ማድረግ ይኖርብናል፤ እንዲህ ሲባል ግን ፍጹም እንሆናለን ማለት አይደለም። (1 ጢሞ. 4:15) በየዕለቱ መንፈሱ የሚሰጠንን አመራር ተከትለን ለመመላለስ ወይም ሕይወታችንን ለመምራት አቅማችን የፈቀደውን ያህል ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። ‘በመንፈስ መመላለስ’ የአምላክን ሞገስ ያስገኛል።​—ገላ. 5:16

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ