የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሁሉም ሰው ነፃ ይሆናል
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 1
    • ‘የእግዚአብሔር ልጆች መገለጥ’

      ይሖዋ፣ ፍጥረት ለከንቱነት እንዲገዛ ያደረገው ወደፊት አንድ ቀን ሰብዓዊው ቤተሰብ የእግዚአብሔር ልጆች በሚፈጽሙት ተግባር አማካኝነት ነፃነት እንደሚጎናጸፍ ‘ተስፋ’ በመስጠት ነው። እነዚህ ‘የእግዚአብሔር ልጆች’ እነማን ናቸው? እንደተቀረው “[ሰብዓዊ] ፍጥረት” በኃጢአትና በአለፍጽምና ባርነት ሥር የተወለዱ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ናቸው። በውልደት ንጹሕና ፍጹም በሆነው የአምላክ ጽንፈ ዓለማዊ ቤተሰብ ውስጥ ለእነሱ የሚገባ ቦታ የለም። ሆኖም ይሖዋ አንድ ልዩ ነገር ያደርግላቸዋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ከወረሱት የኃጢአት ቀንበር ነፃ ያወጣቸዋል፤ እንዲሁም ‘ጻድቃን’ ወይም መንፈሳዊ ንጽሕና ያላቸው ሰዎች አድርጎ ይቆጥራቸዋል። (1 ቆሮንቶስ 6:​11) ከዚያም “የእግዚአብሔር ልጆች” አድርጎ በመቁጠር ወደ ጽንፈ ዓለማዊው ቤተሰብ መልሶ ያመጣቸዋል።​—⁠ሮሜ 8:​14-17

      ይሖዋ ልጆቹ አድርጎ የተቀበላቸው እንደመሆናቸው መጠን ክብራማ መብት ይኖራቸዋል። የአምላክ ሰማያዊ ግዛት ወይም መንግሥት አባላት በመሆን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ‘የአምላካችን ካህናት ሆነው በምድር ላይ ይነግሣሉ።’ (ራእይ 5:​9, 10፤ 14:​1-4) ይህ መንግሥት በጭቆናና በአምባገነንነት ላይ ሳይሆን በነፃነትና በፍትሕ መመሪያዎች ላይ በጥብቅ የተመሠረተ ነው። (ኢሳይያስ 9:​6, 7፤ 61:​1-4) ሐዋርያው ጳውሎስ እነዚህ የአምላክ ልጆች ከረዥም ጊዜ በፊት ተስፋ የተሰጠበት ‘የአብርሃም ዘር’ የሆነው የኢየሱስ ወዳጆች መሆናቸውን ገልጿል። (ገላትያ 3:​16, 26, 29) ስለዚህም አምላክ ለወዳጁ ለአብርሃም የገባውን ቃል በመፈጸም ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የዚህ ተስፋ አንዱ ክፍል በአብርሃም ዘር (ወይም ዝርያ) አማካኝነት ‘የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርግጥ ራሳቸውን የሚባርኩ’ መሆናቸው ነው።​—⁠ዘፍጥረት 22:​18 NW

  • ሁሉም ሰው ነፃ ይሆናል
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 1
    • ‘የእግዚአብሔር ልጆች መገለጥ’ የሚጀምረው መቼ ነው? ይሖዋ የእግዚአብሔር ልጆች እነማን መሆናቸውን ግልጽ በሚያደርግበት ጊዜ በቅርቡ ይሆናል። ይህ የሚሆነው ከሞት ተነሥተው ወደ መንፈሳዊው ዓለም የገቡት እነዚህ “ልጆች” ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በአምላክ የአርማጌዶን ጦርነት ይህችን ምድር ከክፋትና ከጭቆና ነፃ በማውጣቱ ተግባር በሚካፈሉበት ጊዜ ነው። (ዳንኤል 2:​44፤ 7:​13, 14, 27፤ ራእይ 2:​26, 27፤ 16:​16፤ 17:​14፤ 19:​11-21) ወደ ‘መጨረሻዎቹ ቀናት’ ዘልቀን መግባታችንን ማለትም አምላክ ለረዥም ጊዜ ታግሦ የቆየው ዓመፅና የእሱ ውጤት የሆነው ክፋት የሚያበቃበት ጊዜ መቅረቡን የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች በዙሪያችን እንመለከታለን።​—⁠2 ጢሞቴዎስ 3:​1-5፤ ማቴዎስ 24:​3-31

  • ሁሉም ሰው ነፃ ይሆናል
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 1
    • ‘የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ እየተጠባበቅህ’ እየደረሰብህ ያለው መከራና የፍትሕ መጓደል ከአቅምህ በላይ የሆነ በሚመስልህ ጊዜ እንኳ ሐዋርያው ጳውሎስ በክርስቶስ ጥበቃና ድጋፍ ላይ የነበረውን ዓይነት ትምክህት አዳብር። ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር ልጆች መገለጥ ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ እንዲህ ሲል ጠይቋል:- “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፣ ወይስ ጭንቀት፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ራብ፣ ወይስ ራቁትነት፣ ወይስ ፍርሃት፣ ወይስ ሰይፍ ነውን?” (ሮሜ 8:​35) እርግጥ እንደ ሩሶ አባባል በጳውሎስ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች በአንድ መልኩም ይሁን በሌላ በጨቋኝ ኃይሎች “የባርነት ቀንበር” ሥር ይገኙ ነበር። “እንደሚታረዱ በጎች” ‘ቀኑን ሙሉ እንደሚገደሉ’ ሆነው ነበር። (ሮሜ 8:​36) ታዲያ በዚህ ሁኔታ እጃቸውን ሰጡን?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ