የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በተስፋችን ደስ ይበለን
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | መጋቢት 15
    • 10, 11. (ሀ) ሌሎች በጎች ምን ተስፋ ተዘርግቶላቸዋል? (ለ) የሌሎች በጎች ተስፋ ፍጻሜ ከክርስቶስና ‘ከአምላክ ልጆች መገለጥ’ ጋር የተያያዘው እንዴት ነው?

      10 ሐዋርያው ጳውሎስ፣ በመንፈስ የተወለዱ “የአምላክ ልጆች” ‘ከክርስቶስ ጋር የመውረስ’ አስደናቂ ተስፋ እንዳላቸው ጽፏል። በመቀጠልም ይሖዋ፣ ያልተወሰነ ቁጥር ላላቸው ሌሎች በጎች ያዘጋጀውን አስደናቂ ተስፋ አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፦ “[ሰብዓዊው] ፍጥረት የአምላክን ልጆች [ይኸውም የቅቡዓኑን] መገለጥ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠባበቀ ነው። ምክንያቱም ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቷል፤ የተገዛው ግን በገዛ ፈቃዱ ሳይሆን በተስፋ እንዲገዛ ባደረገው በእሱ አማካኝነት ነው፤ ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከመበስበስ ባርነት ነፃ ወጥቶ የአምላክን ልጆች ክብራማ ነፃነት ማግኘት ነው።”​—ሮም 8:14-21

  • በተስፋችን ደስ ይበለን
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | መጋቢት 15
    • 12. የቅቡዓኑ መገለጥ ለሰው ዘር ምን ግሩም በረከቶች ያስገኛል?

      12 ሰብዓዊው “ፍጥረት” በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት በቃላት ሊገለጽ የማይችል እፎይታ ያገኛል! ክብር የተላበሱት ‘የአምላክ ልጆች’ በዚህ ወቅትም በሌላ መንገድ ይገለጣሉ፤ ይህ የሚሆነው ከክርስቶስ ጋር ካህናት በመሆን የሰው ዘር ከኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ጥቅሞች እንዲያገኝ ሲያደርጉ ነው። የሰማያዊው መንግሥት ተገዥ የሆነው ሰብዓዊ “ፍጥረት” ኃጢአትና ሞት ካስከተሏቸው መጥፎ ውጤቶች ነፃ መሆን ይጀምራል። በዚህ መንገድ ታዛዥ የሆኑት የሰው ልጆች ቀስ በቀስ “ከመበስበስ ባርነት ነፃ” ይሆናሉ። በተጨማሪም እስከ ሺው ዓመት ፍጻሜ ድረስ ለይሖዋ ታማኝ ከሆኑና መጨረሻ ላይ የሚቀርበውን ፈተና ካለፉ ስማቸው “የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል” ላይ ለዘላለም ይጻፋል። በዚህ ወቅት ‘የአምላክ ልጆች የመሆን ክብራማ ነፃነት’ ያገኛሉ። (ራእይ 20:7, 8, 11, 12) በእርግጥም ይህ፣ ክብራማ የሆነ ተስፋ ነው!

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ