የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ ዓላማ በሚያስደንቅ ሁኔታ ግቡን ይመታል
    እውነተኛውን አንድ አምላክ አምልክ
    • ወደፊት የሚገኝ አስደናቂ ነፃነት

      11. ከታላቁ መከራ የሚተርፉ ሁሉ ምን አስደናቂ ነፃነት ያገኛሉ?

      11 በአርማጌዶን የሚደመደመው ታላቁ መከራ ምድርን ከክፋት ካጸዳ በኋላ ሰይጣን ዲያብሎስ “የዚህ ዓለም አምላክ” መሆኑ ያከትማል። ከዚያ በኋላ የይሖዋ አምላኪዎች ሰይጣን ከሚያሳድረው መጥፎ ተጽዕኖ ጋር የሚያደርጉት ትግል ያበቃል። (2 ቆሮንቶስ 4:4፤ ራእይ 20:1, 2) በዚያን ጊዜ የይሖዋን ስም የሚያሰድብም ሆነ ሰዎችን የሚከፋፍል የሐሰት ሃይማኖት አይኖርም። የእውነተኛው አምላክ አገልጋዮች በሰብዓዊ ባለ ሥልጣናት የሚደርስባቸው ግፍና በደል ያከትማል። ይህ እንዴት ያለ አስደናቂ ነፃነት ነው!

      12. ሰዎች ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች የሚላቀቁት እንዴት ነው?

      12 ኢየሱስ “የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” ስለሆነ በመሥዋዕቱ ዋጋ አማካኝነት የሰውን ዘር ኃጢአት ይደመስሳል። (ዮሐንስ 1:29) ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት የአንድን ሰው ኃጢአት ይቅር ሲል በእርግጥ ይቅር እንዳለ ለማሳየት ሰውየውን ይፈውሰው ነበር። (ማቴዎስ 9:1-7፤ 15:30, 31) በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቶስ ኢየሱስ የአምላክ ሰማያዊ መንግሥት ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ማየት፣ መናገርና መስማት የተሳናቸውን፣ የአካል ጉዳተኞችን፣ የአእምሮ ሕመም ያለባቸውንና በሌሎች በሽታዎች የሚሠቃዩትን ሁሉ በተአምራዊ መንገድ ይፈውሳል። (ራእይ 21:3, 4) ታዛዥ የሆኑ ሰዎች በሙሉ ‘ከኀጢአት ሕግ’ ነፃ ስለሚሆኑ ሐሳባቸውና ድርጊታቸው እነሱንም ሆነ አምላክን የሚያስደስት ይሆናል። (ሮሜ 7:21-23) በሺው ዓመት ማብቂያ ላይ ወደ ሰብዓዊ ፍጽምና ስለሚደርሱ የእውነተኛውን አንድ አምላክ ‘መልክና አምሳል’ በትክክል ያንጸባርቃሉ።—ዘፍጥረት 1:26

      13. ክርስቶስ በሺው ዓመት ግዛት ማብቂያ ላይ ምን እርምጃ ይወስዳል? ከምንስ ውጤት ጋር?

      13 ክርስቶስ የሰውን ዘር ወደ ፍጽምና ደረጃ ካደረሰ በኋላ ይህን ሥራ ለማከናወን የተሰጠውን ሥልጣን ለአባቱ መልሶ ያስረክባል:- “ግዛትን፣ ሥልጣንና ኀይልን ሁሉ ከደመሰሰ በኋላ መንግሥትን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ፣ ያን ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል። ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።” (1 ቆሮንቶስ 15:24, 25) የመንግሥቱ የሺህ ዓመት አገዛዝ የታለመለትን ዓላማ ሙሉ በሙሉ ዳር ያደርሳል፤ ስለሆነም በይሖዋና በሰዎች መካከል ሆኖ ሲያገለግል የቆየው ይህ መንግሥት ከዚያ በኋላ አያስፈልግም። በተጨማሪም ኃጢአትና ሞት ሙሉ በሙሉ ስለሚወገዱና የሰው ዘር ስለሚዋጅ ኢየሱስ የሰው ልጆችን ለመቤዠት ሲያከናውነው የቆየው አገልግሎት ያበቃል። መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ወልድ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል” ሲል ይገልጻል።—1 ቆሮንቶስ 15:28

      14. ፍጹም የሆኑ ሰዎች ሁሉ ምን እንዲደርስባቸው ይደረጋል? ለምንስ?

      14 ከዚህ በኋላ ፍጹም የሆኑት የሰው ልጆች ምርጫቸው እውነተኛውን አንድ አምላክ ለዘላለም ማገልገል እንደሆነ ማሳየት የሚችሉበት አጋጣሚ ያገኛሉ። በመሆኑም ይሖዋ ፍጹም የሆኑትን የሰው ልጆች ሙሉ በሙሉ ልጆቹ አድርጎ ከመቀበሉ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ እንዲፈተኑ ያደርጋል። ሰይጣንና አጋንንቱ ከጥልቁ ይለቀቃሉ። ይህ ይሖዋን ከልብ በሚወዱ ላይ ዘላቂ ጉዳት አያስከትልም። ሆኖም በይሖዋ ላይ የሚያምጹ ሁሉ ከመጀመሪያው ዓመጸኛ ከሰይጣንና ከአጋንንቱ ጋር ለዘላለም ይጠፋሉ።—ራእይ 20:7-10

      15. የይሖዋ መንፈሳዊና ሰብዓዊ ፍጥረታት ሁሉ ዳግመኛ ምን የሚያደርጉበት ጊዜ ይመጣል?

      15 ይሖዋ በመጨረሻው ፈተና ወቅት የእሱን ሉዓላዊነት የሚደግፉትን ፍጹማን ሰዎች ሁሉ እንደ ልጆቹ አድርጎ ይቀበላቸዋል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የአምላክ ጽንፈ ዓለማዊ ቤተሰብ አባላት በመሆን የአምላክ ልጆች የሚያገኙትን አስደናቂ የሆነ ነፃነት በተሟላ ሁኔታ ይጎናጸፋሉ። በሰማይና በምድር ያሉት መንፈሳዊና ሰብዓዊ ፍጥረታት ሁሉ ዳግመኛ እውነተኛውን አንድ አምላክ አንድ ሆነው ያመልካሉ። የይሖዋ ዓላማ በሚያስደንቅ ሁኔታ ግቡን ይመታል! የዚህ ደስተኛ፣ ዘላለማዊና ጽንፈ ዓለማዊ ቤተሰብ አባል መሆን ትፈልጋለህ? የምትፈልግ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በ⁠1 ዮሐንስ 2:17 ላይ “ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል” በማለት የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ እንድታደርግ እናበረታታሃለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ