-
ከአምላክ ፍቅር ማን ይለየናል?መጠበቂያ ግንብ—2001 | ጥቅምት 15
-
-
14. ክርስቲያኖች መከራ ቢደርስባቸውም ጳውሎስ በአምላክ ፍቅር ላይ ጽኑ እምነት እንዲኖረው ያደረገው ምንድን ነው?
14 ሮሜ 8:38, 39ን አንብብ። ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ምንም ነገር ከአምላክ ፍቅር ሊለያቸው እንደማይችል እርግጠኛ ሊሆን የቻለው ለምንድን ነው? ጳውሎስ በአገልግሎቱ ያጋጠሙት ተሞክሮዎች መከራ አምላክ ለእኛ ፍቅር ማሳየቱን እንዲያቆም ፈጽሞ ሊያደርጉት እንደማይችሉ የነበረውን ጽኑ እምነት እንዳጠናከሩለት ምንም ጥርጥር የለውም። (2 ቆሮንቶስ 11:23-27፤ ፊልጵስዩስ 4:13) እንዲሁም ጳውሎስ የይሖዋን ዘላለማዊ ዓላማና ለጥንት ሕዝቦቹ ያደረገላቸውን ነገሮች ያውቅ ነበር። አምላክ ለታማኝ አገልጋዮቹ ያለው ፍቅር በሞት ድል ሊደረግ ይችል ይሆን? በጭራሽ! በሞት ያንቀላፉት እነዚህ ታማኞች ፍጹም በሆነው በአምላክ አእምሮ ውስጥ የሚታወሱ በመሆናቸው ጊዜው ሲደርስ ከሞት ያስነሳቸዋል።—ሉቃስ 20:37, 38፤ 1 ቆሮንቶስ 15:22-26
-
-
ከአምላክ ፍቅር ማን ይለየናል?መጠበቂያ ግንብ—2001 | ጥቅምት 15
-
-
16 ክርስቲያን እንደመሆናችን መጠን ጳውሎስ “ያለውም ቢሆን” በማለት ከጠራቸው በዚህ ሥርዓት ውስጥ ከሚደርሱ ክስተቶች፣ ሁኔታዎችና ክንውኖች ወይም ወደፊት ሊመጡ ከሚችሉ ነገሮች መካከል አንዱም ቢሆን አምላክ ከሕዝቡ ጋር የመሠረተውን የጠበቀ ግንኙነት እንዲያላላ ሊያደርጉት ይችላሉ ብለን መፍራት አይኖርብንም። ምንም እንኳ ምድራዊና ሰማያዊ ኃይሎች ጦርነት የከፈቱብን ቢሆንም የአምላክ ታማኝ ፍቅር ደግፎ ያቆመናል። ጳውሎስ ጠበቅ አድርጎ እንደገለጸው “ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን” የአምላክን ፍቅር ሊያግድ አይችልም። አዎን፣ ተስፋ ሊያስቆርጥ የሚችል ማንኛውም ነገር ወይም በእኛ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል የትኛውም ኃይል ከአምላክ ፍቅር ሊለየን አይችልም። እንዲሁም ፈጣሪ ከታማኝ አገልጋዮቹ ጋር የመሠረተውን ዝምድና የትኛውም ፍጡር ሊበጥስ አይችልም። የአምላክ ፍቅር ፈጽሞ አይወድቅም፤ ለዘላለም ይኖራል።—1 ቆሮንቶስ 13:8
-