-
አምላክ ማን ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ይሖዋ ስሙን እንድታውቅና እንድትጠቀምበት ይፈልጋል
ይሖዋ ስሙን እንድታውቅ እንደሚፈልግ በምን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ስሙ እንዲታወቅ የሚፈልግ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
ይሖዋ ሰዎች ስሙን እንዲጠቀሙበት ይፈልጋል። ሮም 10:13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ የሚለውን የአምላክ ስም መጠቀም በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
አንድ ሰው ስምህን አስታውሶ ሲጠራህ ምን ይሰማሃል?
ይሖዋ በስሙ ስትጠቀም ምን የሚሰማው ይመስልሃል?
-
-
የሐሰት ሃይማኖቶች የአምላክን ስም ያሰደቡት እንዴት ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. የሐሰት ሃይማኖቶች የሚያስተምሩት ትምህርት አምላክን የሚያሰድበው እንዴት ነው?
የሐሰት ሃይማኖቶች “የአምላክን እውነት በሐሰት ለውጠዋል።” (ሮም 1:25) ለምሳሌ ያህል፣ ብዙ ሃይማኖቶች የአምላክ ስም ማን እንደሆነ ለተከታዮቻቸው አያስተምሩም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የአምላክን ስም መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ይገልጻል። (ሮም 10:13, 14) አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች አንድ መጥፎ ነገር ሲከሰት አምላክ ያመጣው እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም ይህ ውሸት ነው። አምላክ በምንም ዓይነት መጥፎ የሆነ ነገር አያደርግም። (ያዕቆብ 1:13ን አንብብ።) የሚያሳዝነው፣ የሐሰት ሃይማኖቶች የሚያስተምሩት ውሸት ሰዎች ከአምላክ እንዲርቁ አድርጓል።
-