የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ እጅ አላጠረችም
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 17. የጽዮን ታዳጊ ማን ነው? የታደጋትስ መቼ ነው?

      17 በሙሴ ሕግ መሠረት ራሱን ለባርነት የሸጠን አንድ እስራኤላዊ ሌላ ሰው ከባርነት ሊቤዠው ይችል ነበር። ቀደም ሲል በትንቢታዊው የኢሳይያስ መጽሐፍ ውስጥ ይሖዋ ንስሐ የገቡ ሰዎችን የሚታደግ አምላክ እንደሆነ ተገልጾ ነበር። (ኢሳይያስ 48:​17) አሁንም በድጋሚ ንስሐ የገቡ ሰዎችን እንደሚታደግ ተገልጿል። ኢሳይያስ፣ ይሖዋ የገባውን ቃል እንዲህ ሲል ዘግቧል:- “ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፣ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፣ ይላል እግዚአብሔር።” (ኢሳይያስ 59:20) ይህ አጽናኝ ተስፋ በ537 ከዘአበ ተፈጽሟል። ይሁን እንጂ ሌላም ተፈጻሚነት አለው። ሐዋርያው ጳውሎስ እነዚህን ቃላት ከሰፕቱጀንት ትርጉም ላይ በመጥቀስ በክርስቲያኖች ላይ ፍጻሜያቸውን እንደሚያገኙ ጠቁሟል። እንዲህ ሲል ጻፈ:- “እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ:- መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል። ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።” (ሮሜ 11:26, 27) በእርግጥም ይህ የኢሳይያስ ትንቢት በዚያ ዘመን ብቻ ተወስኖ አይቀርም። ከዚህ ይልቅ እኛ ባለንበት ዘመንም ሆነ ወደፊት በስፋት ፍጻሜውን ያገኛል። እንዴት?

  • የይሖዋ እጅ አላጠረችም
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 19. ይሖዋ ከአምላክ እስራኤል ጋር ምን ቃል ኪዳን ገብቷል?

      19 በመቀጠል ይሖዋ ከአምላክ እስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ዘገባው እንዲህ ይላል:- “ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል እግዚአብሔር፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ ከአፍህ ከዘርህም አፍ ከዘር ዘርህም አፍ አያልፍም፣ ይላል እግዚአብሔር።” (ኢሳይያስ 59:21) እነዚህ ቃላት በራሱ በኢሳይያስ ላይ ተፈጻሚነታቸውን አገኙም አላገኙ ‘ዘሩን እንደሚያይ’ ዋስትና ተሰጥቶት በነበረው በኢየሱስ ላይ ፍጻሜያቸውን እንዳገኙ ጥርጥር የለውም። (ኢሳይያስ 53:​10) ኢየሱስ ከይሖዋ የተማረውን ቃል ያስተማረ ሲሆን የይሖዋ መንፈስ በላዩ ነበረ። (ዮሐንስ 1:​18፤ 7:​16) የአምላክ እስራኤል አባላት የሆኑትና ከእርሱ ጋር አብረው የሚወርሱት ወንድሞቹም የይሖዋን ቅዱስ መንፈስ ተቀብለው ሰማያዊ አባታቸው ያስተማራቸውን ቃል መስበካቸው የተገባ ነው። ሁሉም “ከእግዚአብሔር የተማሩ” ናቸው። (ኢሳይያስ 54:​13፤ ሉቃስ 12:​12፤ ሥራ 2:​38) ይሖዋ በሌላ እንደማይተካቸውና ለዘላለም ምሥክሮቹ አድርጎ እንደሚጠቀምባቸው በኢሳይያስ አማካኝነት አሊያም ኢሳይያስ ትንቢታዊ አምሳያ በሆነለት በኢየሱስ በኩል ቃል ገብቷል። (ኢሳይያስ 43:​10) ይሁንና በዚህ ቃል ኪዳን የሚጠቀሙት ‘ዘሮቻቸው’ እነማን ናቸው?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ