-
3 | ጥላቻን ከአእምሮህ ነቅለህ አውጣመጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022 | ቁጥር 1
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦
“ጥሩ የሆነውን፣ ተቀባይነት ያለውንና ፍጹም የሆነውን የአምላክ ፈቃድ መርምራችሁ ማረጋገጥ ትችሉ ዘንድ አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ።”—ሮም 12:2
ምን ማለት ነው?
አምላክ የምናስብበት መንገድ ያሳስበዋል። (ኤርምያስ 17:10) ጥላቻ የሚንጸባረቅበት ነገር መናገር ወይም ማድረግ እንደሌለብን ግልጽ ነው፤ ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም። የጥላቻ ሰንሰለት የሚጀምረው በአእምሮና በልብ ውስጥ ነው። ስለዚህ ጥላቻን ከአስተሳሰባችንም ሆነ ከስሜታችን ነቅለን ማውጣት ይኖርብናል። እውነተኛ ‘ለውጥ’ ማድረግና የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የምንችለው እንዲህ ካደረግን ብቻ ነው።
-