-
“ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ሐምሌ
-
-
14. ሐዘን የደረሰባቸውን ሰዎች ለማጽናናት ምን ማለት እንችላለን?
14 በሐዘን የተዋጠን ሰው ለማጽናናት ምን ማለት እንዳለብን ማወቅ ከባድ ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነው። ያም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ “የጥበበኞች ምላስ . . . ፈውስ ነው” ይላል። (ምሳሌ 12:18) ብዙዎች ሐዘን የደረሰባቸውን ሰዎች ለማጽናናት የሚያስችሉ ሐሳቦችን የምትወዱት ሰው ሲሞት ከተባለው ብሮሹር ላይ አግኝተዋል።c ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ፣ ያዘኑ ሰዎችን ማጽናናት የምትችሉበት ዋነኛው መንገድ “ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ” የሚለውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ነው። (ሮም 12:15) ጋቢ የተባለች ባሏን በሞት ያጣች እህት፣ አንዳንድ ጊዜ ሐዘኗን መግለጽ የምትችለው በማልቀስ ብቻ እንደሆነ ተናግራለች። አክላም “ወዳጆቼ አብረውኝ ማልቀሳቸው የሚያጽናናኝ ለዚህ ነው። እንዲህ ሲያደርጉ ሐዘኔን የሚጋራኝ ሰው እንዳለ ይሰማኛል” ብላለች።
-
-
“ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ሐምሌ
-
-
20. ይሖዋ የሰጣቸው ተስፋዎች በጣም የሚያጽናኑ ናቸው የምንለው ለምንድን ነው?
20 ‘በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ የክርስቶስን ድምፅ ሰምተው በሚወጡበት’ ወቅት፣ የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆነው ይሖዋ ሐዘንን ጨርሶ በማስወገድ ሁሉንም ሰው እንደሚያጽናና ማወቃችን ምንኛ የሚያበረታታ ነው! (ዮሐ. 5:28, 29) መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ “ሞትን ለዘላለም ያስወግዳል፤ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል” የሚል ተስፋ ይሰጣል። (ኢሳ. 25:8 ግርጌ) በዚያ ወቅት የምድር ነዋሪዎች በሙሉ ‘ከሚያለቅሱ ጋር በማልቀስ’ ፋንታ “ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ [ይላቸዋል]።”—ሮም 12:15
-