-
የማያዳላው አምላካችንን ይሖዋን ምሰሉመጠበቂያ ግንብ—2003 | ሰኔ 15
-
-
11. በመጀመሪያው መቶ ዘመን በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ አድልዎ አልነበረም ማለት የሚቻለው እንዴት ነው?
11 በመጀመሪያው መቶ ዘመን በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ አይሁዳውያንም ሆኑ አሕዛብ እኩል ቦታ ነበራቸው። ጳውሎስ “በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፣ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው። እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላምና።”b (ሮሜ 2:10, 11) ከይሖዋ የማይገባ ደግነት ተጠቃሚ መሆናቸው የተመካው በዘር ሐረጋቸው ላይ ሳይሆን ስለ ይሖዋና በልጁ በኢየሱስ ቤዛ አማካኝነት ስለተከፈተላቸው ተስፋ ሲማሩ በሚሰጡት ምላሽ ላይ ነው። (ዮሐንስ 3:16, 36) ጳውሎስ “በግልጥ አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና፣ በግልጥ በሥጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና፤ ዳሩ ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፣ መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም” በማለት ጽፏል። ከዚያም “አይሁዳዊ” (“የይሁዳ ወገን” ማለት ሲሆን የተመሰገነ ወይም የተወደሰ የሚል ትርጉም አለው) የሚለውን ቃል ፍቺ በመጠቀም “የእርሱ ምስጋና ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም” በማለት ተናግሯል። (ሮሜ 2:28, 29) ይሖዋ የሚያመሰግነው ያለ አድልዎ ነው። እኛስ?
-
-
የማያዳላው አምላካችንን ይሖዋን ምሰሉመጠበቂያ ግንብ—2003 | ሰኔ 15
-
-
b በዚህ አገባቡ “ግሪካዊ” የሚለው ቃል አሕዛብን በጠቅላላ ያመለክታል።—በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 1004 ተመልከት።
-