-
ቁጣችሁን በመቆጣጠር ‘ምንጊዜም ክፉውን አሸንፉ’መጠበቂያ ግንብ—2010 | ሰኔ 15
-
-
10. ክርስቲያኖች በቀልን በተመለከተ ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?
10 ከስምዖንና ከሌዊ እንዲሁም ከዳዊትና ከአቢግያ ሁኔታ በግልጽ መመልከት እንደምንችለው ይሖዋ ልጓም ያልተበጀለት ቁጣንና ዓመፅን የሚቃወም ሲሆን ሰላም ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶችን ግን ይባርካል። ሐዋርያው ጳውሎስ “ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ” በማለት ጽፏል። አክሎም “የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ከዚህ ይልቅ ‘በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ይላል ይሖዋ’ ተብሎ ስለተጻፈ ለአምላክ ቁጣ ዕድል ስጡ። ነገር ግን ‘ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ የሚጠጣ ነገር ስጠው፤ ይህን በማድረግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ።’ በክፉ አትሸነፍ፤ ከዚህ ይልቅ ምንጊዜም ክፉውን በመልካም አሸንፍ።”—ሮም 12:18-21a
-
-
ቁጣችሁን በመቆጣጠር ‘ምንጊዜም ክፉውን አሸንፉ’መጠበቂያ ግንብ—2010 | ሰኔ 15
-
-
a ‘ፍም መከመር’ የሚለው አገላለጽ በጥንት ዘመን ከነበረው ያልተጣራ ብረትን የማቅለጥ ዘዴ የተወሰደ ነው። ብረቱን ከቆሻሻው ለመለየት ከላይም ከታችም ፍም ይደረግበታል። እኛም በተመሳሳይ ደግነት የጎደለው ድርጊት ለሚፈጽሙ ሰዎች ደግነት ማሳየታችን አመለካከታቸው እንዲለወጥና መልካም ባሕርያቸው ጎልቶ እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላል።
-