የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ’
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥቅምት 15
    • ክፉውን በመልካም ማሸነፍ

      13, 14. (ሀ) ተቃውሞ ሲያጋጥመን ግራ የማንጋባው ለምንድን ነው? (ለ) የሚያሳድዱንን ሰዎች መባረክ የምንችለው እንዴት ነው?

      13 ሮም 12:14, 21⁠ን አንብብ። ይሖዋ ዓላማዎቹን እንደሚፈጽም ሙሉ በሙሉ በመተማመን እሱ እንድናከናውነው በሰጠን ተልእኮ ማለትም “በመላው ምድር” ላይ ‘የመንግሥቱን ምሥራች’ በመስበኩ ሥራ በተሟላ መንገድ ለመካፈል ጥረት ማድረግ እንችላለን። (ማቴ. 24:14) ኢየሱስ “በስሜ ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” በማለት ስላስጠነቀቀን የምናከናውነው ክርስቲያናዊ እንቅስቃሴ ጠላቶቻችንን እንደሚያስቆጣቸው እናውቃለን። (ማቴ. 24:9) በመሆኑም ተቃውሞ ሲያጋጥመን ግራ አንጋባም ወይም ተስፋ አንቆርጥም። ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እንደ እሳት በሚያቃጥሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ስትፈተኑ እንግዳ የሆነ ነገር እንደደረሰባችሁ አድርጋችሁ በማሰብ ግራ አትጋቡ። ከዚህ ይልቅ ክርስቶስ . . . የተቀበለው መከራ ተካፋዮች በሆናችሁበት በዚያው መጠን ምንጊዜም ደስ ይበላችሁ።”—1 ጴጥ. 4:12, 13

  • ‘ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ’
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥቅምት 15
    • 15. ክፉውን በመልካም ለማሸነፍ ከሁሉ የተሻለው መንገድ የትኛው ነው?

      15 ከላይ ከተመለከትነው አንጻር አንድ እውነተኛ ክርስቲያን በ⁠ሮም ምዕራፍ 12 የመጨረሻ ቁጥር ላይ የሚገኘውን “በክፉ አትሸነፍ፤ ከዚህ ይልቅ ምንጊዜም ክፉውን በመልካም አሸንፍ” የሚለውን ምክር ተግባራዊ ያደርጋል። የክፋት ሁሉ ምንጭ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው። (ዮሐ. 8:44፤ 1 ዮሐ. 5:19) ለሐዋርያው ዮሐንስ በተሰጠው ራእይ ላይ ኢየሱስ፣ ቅቡዓን ወንድሞቹ ‘ከበጉ ደም የተነሳና ከምሥክርነታቸው ቃል የተነሳ ሰይጣንን ድል እንደነሱት’ ገልጧል። (ራእይ 12:11) ይህም ሰይጣንንም ሆነ በዚህ ሥርዓት ላይ የሚያሳድረውን መጥፎ ተጽዕኖ ድል መንሳት የሚቻልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ በምሥክርነቱ ሥራ መልካም ማድረግ ማለትም የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ እንደሆነ ያሳያል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ