የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከፍተኛና አነስተኛ የብርሃን ብልጭታዎች (ክፍል ሁለት)
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ግንቦት 15
    • “ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት” እነማን እንደሆኑ ተብራራ

      4, 5. (ሀ) የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ስለ ሮሜ 13:1 ምን አመለካከት ነበራቸው? (ለ) “ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት” ያላቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ቦታ በተመለከተ ቆየት ብሎ ምን ማስተዋል ተገኝቶ ነበር?

      4 በ1962 “ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች [“ለከፍተኛ ባለ ሥልጣናት” ኪንግ ጀምስ ቨርሽን] ይገዛ” ከሚለው ከሮሜ 13:1 ጋር በተያያዘ መንገድ ደማቅ የብርሃን ብልጭታ ታየ። የቀድሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በዚህ ጥቅስ ላይ “ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት” ተብለው የተጠቀሱት ዓለማዊ ባለ ሥልጣናት እንደሆኑ ተረድተው ነበር። ይህን ጥቅስ የተረዱት አንድ ክርስቲያን በጦርነት ወቅት ለወታደርነት ከተመለመለ የደንብ ልብስ ለመልበስ፣ ጠመንጃ ለማነገትና ወደ ጦር ግንባር ዘምቶ ምሽግ ለመያዝ ይገደዳል ማለት እንደሆነ አድርገው ነበር። አንድ ክርስቲያን ሰዎችን መግደል ስለማይችል ከአቅሙ በላይ የሆነ ችግር ካጋጠመው ወደ ሰማይ ለመተኮስ ይገደዳል የሚል ስሜት ነበራቸው።a

      5 የኅዳር 15 እና የታኅሣሥ 1, 1962 መጠበቂያ ግንብ በማቴዎስ 22:21 ላይ “የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” የሚሉትን የኢየሱስ ቃላት በማብራራት በዚህ ጉዳይ ላይ ብሩህ የሆነ ብርሃን ፈንጥቋል። “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል” የሚሉት በሥራ 5:29 ላይ የሚገኙት የሐዋርያት ቃላት ከዚህ ጋር ይስማማሉ። ክርስቲያኖች ለቄሣር ማለትም “ለከፍተኛ ባለ ሥልጣናት” የሚገዙት ከአምላክ ሕግ ጋር የሚጻረር ነገር እስካልተጠየቁ ድረስ ነው። ለቄሣር የምንገዛው በአንፃራዊ መንገድ እንጂ ሙሉ በሙሉ እንዳልሆነ ተስተውሎ ነበር። ክርስቲያኖች የቄሣርን ለቄሣር የሚከፍሉት ነገሩ አምላክ ካወጣቸው ብቃቶች ጋር ካልተጋጨ ብቻ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ ማስተዋል ማግኘት ምንኛ የሚያስደስት ነበር!

  • ከፍተኛና አነስተኛ የብርሃን ብልጭታዎች (ክፍል ሁለት)
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ግንቦት 15
    • a ከዚህ አመለካከት በተቃራኒ በሰኔ 1 እና ሰኔ 15, 1929 የታተመው መጠበቂያ ግንብ “ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት” ተብለው የተጠሩት ይሖዋና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆኑ አብራርቶ ነበር። በ1962 በመጀመሪያ ደረጃ የታረመው ይህ አቋም ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ