የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ከእውነት መሠረታዊ ገጽታዎች’ ትምህርት ማግኘት
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
    • ‘ከእውነት መሠረታዊ ገጽታዎች’ ትምህርት ማግኘት

      “በሕጉ ውስጥ ያለውን እውቀትና እውነት መሠረታዊ ገጽታዎች [ታውቃላችሁ]።”​—ሮም 2:20

  • ‘ከእውነት መሠረታዊ ገጽታዎች’ ትምህርት ማግኘት
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 15
    • 1. የሙሴ ሕግ ምን ትርጉም እንዳለው መረዳታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት የጻፋቸው ደብዳቤዎች ባይኖሩ ኖሮ የሙሴ ሕግ የተለያዩ ገጽታዎች ምን ትርጉም እንዳላቸው መረዳት አንችልም ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “ታማኝ ሊቀ ካህናት” የሆነው ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ “የማስተሰረያ መሥዋዕት” በማቅረብ፣ በቤዛው ላይ እምነት እንዳላቸው በተግባር ለሚያሳዩ ሰዎች “ዘላለማዊ መዳን” ያስገኘላቸው እንዴት እንደሆነ ግልጽ አድርጓል። (ዕብ. 2:17፤ 9:11, 12) ጳውሎስ የመገናኛው ድንኳን ‘ለሰማያዊ ነገሮች ጥላ’ እንደሆነ ብሎም ኢየሱስ መካከለኛ የሆነለት ቃል ኪዳን ሙሴ መካከለኛ ከሆነለት ቃል ኪዳን ጋር ሲነጻጸር ‘የተሻለ’ እንደሆነ ገልጿል። (ዕብ. 7:22፤ 8:1-5) በጳውሎስ ዘመን ሕጉን አስመልክቶ የሚሰጡ እንዲህ ያሉ ማብራሪያዎች እጅግ አስፈላጊ ነበሩ፤ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። እነዚህ ማብራሪያዎች አምላክ ያደረገልን ዝግጅት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ በተሟላ ሁኔታ ለመረዳት ያስችሉናል።

      2. አይሁዳዊ የሆኑ ክርስቲያኖች ከአሕዛብ ከመጡት ይልቅ ምን የተሻለ አጋጣሚ ነበራቸው?

      2 ጳውሎስ ለሮም ክርስቲያኖች በላከው ደብዳቤ ላይ ያሉትን አንዳንድ ሐሳቦች በቀጥታ የጻፈው በትውልድ አይሁዳዊ ለነበሩና በሙሴ ሕግ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ለተማሩ የጉባኤው አባላት ነው። እነዚህ ክርስቲያኖች ከመለኮታዊው ሕግ ጋር ትውውቅ ስላላቸው ይሖዋንና የእሱን የጽድቅ መሠረታዊ ሥርዓቶች በተመለከተ ‘የእውቀትንና የእውነትን መሠረታዊ ገጽታዎች’ የማወቅ አጋጣሚያቸው ሰፊ መሆኑን ጳውሎስ ተገንዝቦ ነበር። አይሁዳዊ የሆኑ ክርስቲያኖች ‘የእውነትን መሠረታዊ ገጽታዎች’ መረዳታቸውና ለእነዚህ ነገሮች ጥልቅ አክብሮት ማሳደራቸው ይሖዋ ለሕዝቡ የሰጠውን ሕግ ለማያውቁ ሰዎች ጥቅም አስገኝቷል። ምክንያቱም፣ እንደ ጥንቶቹ ታማኝ አይሁዳውያን ሁሉ እነዚህ ክርስቲያኖችም ሕጉን ለማያውቁ አሕዛብ እውነትን ማስተማርና ማስረዳት ችለዋል።​—ሮም 2:17-20⁠ን አንብብ።

      ለኢየሱስ መሥዋዕት ጥላ የሆኑ ነገሮች

      3. የጥንቶቹ አይሁዳውያን ያቀርቧቸው ስለነበሩ መሥዋዕቶች ማጥናታችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?

      3 ዛሬም ቢሆን የይሖዋን ዓላማዎች ለመረዳት ከፈለግን ጳውሎስ ስለጠቀሳቸው የእውነት መሠረታዊ ገጽታዎች ማወቃችን እጅግ አስፈላጊ ነው። ከሙሴ ሕግ በስተጀርባ ያሉት መሠረታዊ ሥርዓቶች በአሁኑ ጊዜም ቢሆን ጠቃሚ ናቸው። ይህን በአእምሯችን በመያዝ የሕጉን አንድ ገጽታ ይኸውም መሥዋዕቶችን ከማቅረብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን እንመለከታለን። በሌላ አባባል እነዚህ መሥዋዕቶች ትሑት የሆኑ አይሁዳውያንን ወደ ክርስቶስ የመሯቸውና አምላክ ከእነሱ ስለሚጠብቀው ነገር እንዲገነዘቡ የረዷቸው እንዴት እንደሆነ እናያለን። በተጨማሪም አምላክ መሥዋዕቶችን አስመልክቶ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ሕግጋት ለአምላክ የምናቀርበውን ቅዱስ አገልግሎት ጥራት ለመመርመር የሚረዱን እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን፤ ምክንያቱም ይሖዋ ከአገልጋዮቹ የሚጠብቀው መሠረታዊ ነገር ፈጽሞ አይለወጥም።​—ሚል. 3:6

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ