የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን መማርና ማስተማር
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • 6, 7. (ሀ) በመጀመሪያ ራሳችንን ማስተማር የሚገባን ለምንድን ነው? (ለ) የመጀመሪያው መቶ ዘመን አይሁዳውያን አስተማሪዎች መሆን ያልቻሉት ከምን አንጻር ነው?

      6 በመጀመሪያ ራሳችንን ማስተማር ይገባናል የሚባለው ለምንድን ነው? ራሳችንን ካላስተማርን ሌሎችን በሚገባ ማስተማር ስለማንችል ነው። ጳውሎስ በዘመኑ የነበሩት አይሁዳውያን ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያደርግ አንድ ሐሳብ በመሰንዘር ይህን ሐቅ ጎላ አድርጎ የገለጸ ሲሆን ይህ ዛሬ ላሉት ክርስቲያኖችም ትልቅ መልእክት ይዟል። እንዲህ ሲል ጠየቀ:- “እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን? አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህን? በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን?”​​—⁠⁠ሮሜ 2:​21-23

      7 ጳውሎስ በእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ አሥርቱ ትእዛዛት በቀጥታ ከሚያወግዛቸው ኃጢአቶች መካከል ሁለቱን ማለትም አትስረቅ እና አታመንዝር የሚሉትን ጠቅሷል። (ዘጸአት 20:​14, 15) በጳውሎስ ዘመን የነበሩ አንዳንድ አይሁዳውያን የአምላክን ሕግ በመቀበላቸው በጣም ይኩራሩ ነበር። ‘ሕጉን ስለተማሩ የዕውሮች መሪ፣ በጨለማ ላሉ ብርሃን እንዲሁም የሕፃናት መምህር እንደሆኑ አድርገው’ ራሳቸውን ይቆጥሩ ነበር። (ሮሜ 2:​17-20) ይሁን እንጂ አንዳንዶቹ በስውር ይሰርቁ ወይም ያመነዝሩ ስለነበር ግብዞች ሆነዋል። ይህ ደግሞ ሕጉንም ሆነ በሰማይ የሚኖረውን ሕግ አውጪ የሚያስነቅፍ ነበር። ጳውሎስ የተናገራቸው ቃላት በዘመኑ የነበሩ አንዳንድ አይሁዳውያን ሕጉንና ይሖዋ አምላክን እንዳሰደቡ ያሳያል። ሌላውን ለማስተማር ብቁ መሆን ይቅርና ራሳቸውን ማስተማር እንዳልቻሉ ከዚህ መረዳት ትችላለህ።

      8. በጳውሎስ ዘመን የነበሩ አንዳንድ አይሁዳውያን ‘ቤተ መቅደስ የዘረፉት’ እንዴት ሊሆን ይችላል?

      8 ጳውሎስ ቤተ መቅደስን ስለ መዝረፍ ጠቅሷል። አንዳንድ አይሁዳውያን ቃል በቃል እንዲህ አድርገዋል? ጳውሎስ ይህን ሲል ምን ማለቱ ነበር? ጥቅሱ ዝርዝር ሐሳብ ስለማይሰጥ አንዳንድ አይሁዳውያን እንዴት ‘ቤተ መቅደስ ይዘርፉ’ እንደነበረ በእርግጠኝነት መናገር አንችልም። የኤፌሶን ከተማ ጸሐፊ ቀደም ሲል የጳውሎስ ጓደኞች ‘የቤተ መቅደስ ዕቃ’ አለመስረቃቸውን መናገሩ አይሁዳውያንን በዚህ ድርጊት የሚወነጅሉ አንዳንድ ሰዎች እንደነበሩ ያሳያል። (ሥራ 19:​29-37) ድል አድራጊዎች ወይም ቀናኢ ሃይማኖተኞች ከአረማዊ ቤተ መቅደሶች ዘርፈው ያመጧቸውን ውድ ዕቃዎች አይሁዳውያኑ ለግል ጥቅማቸው ያውሉ ወይም ለሽያጭ ያቀርቡ ነበር? የአምላክ ሕግ በሚያዘው መሠረት በወርቅም ሆነ በብር የተሠሩ ጣዖታት በእሳት መቃጠል እንጂ ለግል ጥቅም መዋል የለባቸውም። (ዘዳግም 7:​25)a ስለሆነም ጳውሎስ፣ የአምላክን ትእዛዝ በመጣስ ከአረማዊ ቤተ መቅደሶች የተወሰዱ ዕቃዎችን ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ ወይም የሸጡ አይሁዳውያን መኖራቸውን በተዘዋዋሪ መጥቀሱ ሊሆን ይችላል።

      9. ኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ እንደ መዝረፍ ሊቆጠሩ የሚችሉ ምን መጥፎ ድርጊቶች ተፈጽመዋል?

      9 በሌላ በኩል ጆሴፈስ ሮም ውስጥ አራት አይሁዳውያን ስለፈጸሙት የዝርፊያ ቅሌት ተናግሯል። የቡድኑ መሪ የሕጉ አስተማሪ የነበረ ሰው ነው። እነዚህ አራት ሰዎች ወደ ይሁዲነት የተለወጠች አንዲት ሮማዊት ሴት በኢየሩሳሌም ለሚገኘው ቤተ መቅደስ ወርቅና ሌሎች ውድ ዕቃዎች በስጦታ መልክ እንድትሰጥ አግባብተው ተቀበሏት። ዕቃዎቹን እጃቸው ካስገቡ በኋላ ለግል ጥቅማቸው አዋሉት። ይህ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ከመዝረፍ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።b ሌሎች ደግሞ እንከን ያለባቸውን መሥዋዕቶች በማቅረብ እንዲሁም በአምላክ ቤተ መቅደስ አደባባይ ውስጥ ስግብግብነት የተሞላበት ንግድ በማካሄድ ቦታውን “የወንበዴዎች ዋሻ” በማድረጋቸው የአምላክን ቤት ዘርፈዋል ሊባል ይችላል።​​—⁠⁠ማቴዎስ 21:​12, 13፤ ሚልክያስ 1:​12-14፤ 3:​8, 9

  • ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን መማርና ማስተማር
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • a ጆሴፈስ አይሁዳውያን ለቅዱስ ነገሮች አክብሮት እንዳላቸው አድርጎ ቢገልጽም የአምላክን ሕግ እንዲህ በማለት አስቀምጦታል:- “ማንኛውም ሰው ሌሎች ከተሞች የሚያመልኳቸውን አማልክት መስደብ ወይም ቤተ መቅደሶቻቸውን መዝረፍ ወይም ለየትኛውም አምላክ የተሰጡ ንዋየ ቅዱሳትን መውሰድ የለበትም።” (በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።)​​—⁠⁠ጁዊሽ አንቲኩዊቲስ ጥራዝ 4፣ ምዕራፍ 8፣ አንቀጽ 10

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ