-
‘ለደስታችን ከእኛ ጋር አብረው የሚሠሩት’ ክርስቲያን ሽማግሌዎችመጠበቂያ ግንብ—2013 | ጥር 15
-
-
6, 7. (ሀ) ሽማግሌዎች የኢየሱስን፣ የጳውሎስንና የሌሎች የአምላክ አገልጋዮችን ምሳሌ መከተል የሚችሉበት አንደኛው መንገድ ምንድን ነው? (ለ) ወንድሞቻችን ስማቸውን አስታውሰን ስንጠራቸው ይበልጥ የሚደሰቱት ለምንድን ነው?
6 በርካታ ወንድሞችና እህቶች፣ ሽማግሌዎች በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ስለሰጧቸው ደስታቸው እንደጨመረ ገልጸዋል። ሽማግሌዎች ይህን ማድረግ የሚችሉበት አንዱ መንገድ ዳዊት፣ ኤሊሁና ኢየሱስ የተዉትን ምሳሌ መከተል ነው። (2 ሳሙኤል 9:6ን፣ ኢዮብ 33:1ን እና ሉቃስ 19:5ን አንብብ።) እነዚህ የይሖዋ አገልጋዮች ሰዎችን በስማቸው በመጥራት ለእነሱ ያላቸውን ልባዊ አሳቢነት አሳይተዋል። ጳውሎስም ቢሆን የእምነት ባልንጀሮቹን ስም ማወቅና አስታውሶ መጥራት ያለውን ጥቅም ተገንዝቧል። ከደብዳቤዎቹ መካከል አንዱን የደመደመው ከ25 የሚበልጡ ወንድሞችንና እህቶችን በስማቸው ጠቅሶ ሰላምታ በመስጠት ነው፤ ከእነዚህ መካከል “የምንወዳትን ጰርሲስን ሰላም በሉልኝ” በማለት የጠቀሳት እህት ትገኝበታለች።—ሮም 16:3-15
-
-
‘ለደስታችን ከእኛ ጋር አብረው የሚሠሩት’ ክርስቲያን ሽማግሌዎችመጠበቂያ ግንብ—2013 | ጥር 15
-
-
8. ጳውሎስ የይሖዋንና የኢየሱስን ምሳሌ ከተከተለባቸው መንገዶች አንዱ የትኛው ነው?
8 ጳውሎስ ሌሎችን ከልቡ በማመስገንም አሳቢነት አሳይቷል፤ ይህ ደግሞ የእምነት ባልንጀሮቹ ደስታ እንዲጨምር ከሚያደርጉ ዋና ዋና መንገዶች መካከል ሌላኛው ነው። በዚህም የተነሳ ለወንድሞቹ ደስታ ከእነሱ ጋር አብሮ እንደሚሠራ በጠቀሰበት ደብዳቤ ላይ “በእናንተ በጣም እኮራለሁ” በማለት ጽፏል። (2 ቆሮ. 7:4) እነዚህ የምስጋና ቃላት የቆሮንቶስን ጉባኤ ወንድሞች በጣም እንዳስደሰቷቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ጳውሎስ ለሌሎች ጉባኤዎችም ተመሳሳይ የምስጋና ቃላት ተናግሯል። (ሮም 1:8፤ ፊልጵ. 1:3-5፤ 1 ተሰ. 1:8) እንዲያውም ለሮም ጉባኤ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ስለ ጰርሲስ ሲናገር “በጌታ ሥራ ብዙ የደከመችው” ብሏታል። (ሮም 16:12) ታማኝ የሆነችው ይህች እህት እነዚህን የአድናቆት ቃላት ስትሰማ ምን ያህል ተደስታ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል! ጳውሎስ ሌሎችን በማመስገን ረገድ የይሖዋንና የኢየሱስን ምሳሌ ተከትሏል።—ማርቆስ 1:9-11ን እና ዮሐንስ 1:47ን አንብብ፤ ራእይ 2:2, 13, 19
-