-
በፍርድ ዙፋኑ ፊት የምትቀርበው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
12 በዚህም ምክንያት ዳንኤል አምላክ ‘በዙፋን ላይ ተቀምጦ’ መመልከቱ አምላክ ፍርድ ለመስጠት መምጣቱን ያመለክታል። ቀደም ሲል ዳዊት “[ይሖዋ ሆይ] ፍርዴንና በቀሌን አድርገህልኛልና፤ ጽድቅን እየፈረድህ በዙፋንህ ላይ ተቀመጥህ” በማለት ዘምሮ ነበር። (መዝሙር 9:4, 7) በተጨማሪም ኢዩኤል “አሕዛብ ይነሡ፣ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፤ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ [እኔ ይሖዋ] በዚያ እቀመጣለሁና” በማለት ጽፏል። (ኢዩኤል 3:12፤ ከኢሳይያስ 16:5 ጋር አወዳድር።) ኢየሱስና ጳውሎስ ሰዎች ክሶችን ለመስማትና ፍርድ ለመስጠት በተቀመጡባቸው ቦታዎች ለፍርድ ቀርበው ነበር።b—ዮሐንስ 19:12–16፤ ሥራ 23:3፤ 25:6
-
-
በፍርድ ዙፋኑ ፊት የምትቀርበው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
b እርስ በርሳቸው ተካሰው ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ክርስቲያኖችን በተመለከተ ጳውሎስ “በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን?” በማለት ጠይቋቸው ነበር።—1 ቆሮንቶስ 6:4
-