የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ወጣቶች ሆይ፣ ምርጫችሁ ይሖዋን ማገልገል ይሁን
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ሐምሌ 1
    • በግለሰብ ደረጃ ራስን መወሰን ያስፈልጋል

      3, 4. ሕይወታቸውን ለአምላክ የወሰኑ ወላጆች ያሏቸው ልጆች በፈቃደኝነት ራሳቸውን ለይሖዋ እንዲወስኑ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

      3 አምላክ፣ አንዱ ወላጃቸው ብቻ እንኳን ታማኝ ክርስቲያን ቢሆን ሕፃናትን ቅዱስ አድርጎ እንደሚመለከታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል። (1 ቆሮንቶስ 7:14) ነገር ግን ይህ ሁኔታ ልጆቹ ለይሖዋ የተወሰኑ አገልጋዮች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል? በጭራሽ። ሆኖም ራሳቸውን ለይሖዋ የወሰኑ ወላጆች ያሳደጓቸው ልጆች በፈቃደኝነት ለአምላክ ራሳቸውን እንዲወስኑ የሚረዳቸውን ሥልጠና ያገኛሉ። ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን እንዲህ በማለት ጽፏል:- “ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ትእዛዝ አክብር፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው። . . . በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤ በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል። እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤ ይህችም ትምህርት ብርሃን፣ የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት።”—ምሳሌ 6:20-23

  • ወጣቶች ሆይ፣ ምርጫችሁ ይሖዋን ማገልገል ይሁን
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ሐምሌ 1
    • ኃላፊነትህን መቀበል

      12. (ሀ) ወላጆች ልጆቻቸውን ማሠልጠን ቢችሉም ምን ሊያደርጉላቸው አይችሉም? (ለ) አንድ ወጣት ለሚያደጋቸው ምርጫዎች በይሖዋ ዘንድ ተጠያቂ የሚሆነው መቼ ነው?

      12 ወጣቶች ሆይ፣ ወላጆቻችሁ ታማኝ የይሖዋ አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት የምታገኙት ጥበቃ የሚያበቃበት ወቅት አለ። (1 ቆሮንቶስ 7:14) ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ እንዳለበት እያወቀ የማያደርግ ሰው ኀጢአት ያደርጋል” ብሎ ጽፏል። (ያዕቆብ 4:17) ወላጆች ለልጆቻቸው ሲሉ አምላክን ማገልገል አይችሉም፤ ልጆችም እንዲሁ ለወላጆቻቸው ሲሉ አምላክን ሊያገለግሉ አይችሉም። (ሕዝቅኤል 18:20) ስለ ይሖዋና ስለ ዓላማዎቹ ትምህርት ቀስማችኋል? የተማራችሁትን ነገር መረዳትና ከአምላክ ጋር የግል ዝምድና መመሥረት በምትችሉበት ዕድሜ ላይ ደርሳችኋል? እንዲህ ከሆነ አምላክ እርሱን ለማገልገል መወሰን እንደምትችሉ አድርጎ እንደሚመለከታችሁ ማሰቡ ምክንያታዊ አይደለም?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ