የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሰብዓዊ ድክመቶችን ማሸነፍ
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መጋቢት 15
    • 4. በ1 ቆሮንቶስ 10:​12, 13 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ጳውሎስ የሰጠው ምክር ምንድን ነው?

      4 ጳውሎስ ልቅ በሆነ ሥነ ምግባር በምትታወቀው በቆሮንቶስ ከተማ ይኖሩ ለነበሩ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ፈተና እና ኃጢአት ያላቸውን ኃይል በተመለከተ ትክክለኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። እንዲህ አለ:- “ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ። ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፣ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።” (1 ቆሮንቶስ 10:​12, 13) ወጣትም ሆንን በዕድሜ የገፋን፣ ወንድም ሆንን ሴት ሁላችንም በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ ወይም በሌላ አካባቢ የተለያዩ ፈተናዎች ይገጥሙናል። ስለዚህ የጳውሎስን ቃላት እንመርምርና ለእኛ ምን ትርጉም እንዳላቸው እንመልከት።

  • ሰብዓዊ ድክመቶችን ማሸነፍ
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መጋቢት 15
    • 7. ሌሎች ፈተናን ተቋቁመው እንዳሸነፉ ማወቁ የሚያጽናና የሆነው ለምንድን ነው?

      7 “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም” የሚሉት የጳውሎስ ቃላት ምንኛ የሚያጽናኑ ናቸው! (1 ቆሮንቶስ 10:​13) ሐዋርያው ጴጥሮስ “በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ [ዲያብሎስን] ተቃወሙት” በማለት ጽፏል። (1 ጴጥሮስ 5:​9) አዎን፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ፈተናዎች ደርሰውባቸው በአምላክ እርዳታ በተሳካ ሁኔታ ተቋቁመዋቸዋል። እኛም ልንቋቋማቸው እንችላለን። ይሁን እንጂ ብልሹ በሆነ ዓለም ውስጥ የምንኖር እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ሁላችንም ፈተና እንደሚደርስብን ልንጠብቅ እንችላለን። ታዲያ ሰብዓዊ ድክመትንና ኃጢአት እንድንሠራ የሚደርስብንን ፈተና በድል እንደምንወጣ እንዴት እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ