የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጥሩ ውሳኔ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 5. የሌሎችን ሕሊና አክብር

      ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ የተለያየ ውሳኔ ሊያደርጉ ይችላሉ። ታዲያ የሌሎችን ሕሊና እንደምናከብር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? እስቲ ሁለት ሁኔታዎችን እንደ ምሳሌ እንመልከት፦

      ምሳሌ 1፦ መኳኳል የምትወድ አንዲት እህት ወደ ሌላ ጉባኤ ተዛወረች፤ በአዲሱ ጉባኤዋ ያሉ ብዙ እህቶች መኳኳል ተገቢ እንደሆነ አይሰማቸውም።

      ሮም 15:1⁠ን እና 1 ቆሮንቶስ 10:23, 24⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት እህት ምን ውሳኔ ልታደርግ ትችላለች? አንተ ሕሊናህ የሚፈቅድልህን ነገር ሌላ ሰው ሕሊናው የማይፈቅድለት ከሆነ ምን ታደርጋለህ?

      ምሳሌ 2፦ አንድ ወንድም፣ በመጠኑ እስከሆነ ድረስ የአልኮል መጠጥ መጠጣትን መጽሐፍ ቅዱስ እንደማይከለክል ያውቃል። ያም ሆኖ ጨርሶ አልኮል ላለመጠጣት ወስኗል። ይህ ወንድም አንድ ግብዣ ላይ ተገኝቶ ወንድሞች የአልኮል መጠጥ ሲጠጡ ይመለከታል።

      መክብብ 7:16⁠ን እና ሮም 14:1, 10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት ወንድም ምን ውሳኔ ሊያደርግ ይችላል? አንተ ሕሊናህ የማይፈቅድልህን ነገር ሌላ ሰው ሲያደርግ ብታይ ምን ታደርጋለህ?

      ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የሚያስችሉ እርምጃዎች

      እየጸለየች ያለች ሴት

      1. ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ እንዲረዳህ ይሖዋን ለምን።—ያዕቆብ 1:5

      ይህችው ሴት መጽሐፍ ቅዱስን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችንና ኮምፒውተሯን ተጠቅማ ምርምር ስታደርግ

      2. ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መሠረታዊ ሥርዓቶች ለማግኘት በመጽሐፍ ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረቱ ጽሑፎች ላይ ምርምር አድርግ። ተሞክሮ ያላቸውን ክርስቲያኖችም ማማከር ትችላለህ።

      ይህችው ሴት ስታስብ

      3. የምታደርገው ውሳኔ በአንተም ሆነ በሌሎች ሕሊና ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ አስብ።

  • የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?—ክፍል 1
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 6. በትዳራችሁ ውስጥ የሚያጋጥማችሁን ችግር መፍታት ትችላላችሁ

      ፍጹም የሆነ ትዳር የለም። በመሆኑም ባለትዳሮች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ተባብረው መሥራት ይኖርባቸዋል። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ የትዳርን ጥምረት ማጠናከር የሚቻለው እንዴት ነው? (5:44)

      • በቪዲዮው ላይ የታዩት ባልና ሚስት እየተራራቁ እንደመጡ የሚያሳዩ አንዳንድ ምልክቶች የትኞቹ ናቸው?

      • ትዳራቸውን ለማጠናከር ምን እርምጃዎች ወሰዱ?

      አንደኛ ቆሮንቶስ 10:24⁠ን እና ቆላስይስ 3:13⁠ን አንብቡ። እያንዳንዱን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ትዳርን ለማጠናከር የሚረዳው እንዴት ነው?

      መጽሐፍ ቅዱስ አንዳችን ሌላውን ማክበር እንዳለብን ይናገራል። ሌሎችን ማክበር ደግነት ማሳየትንም ይጨምራል። ሮም 12:10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • ባሎችም ሆኑ ሚስቶች የትዳር ጓደኛቸው ቀድሞ አክብሮት እስኪያሳያቸው መጠበቅ ይኖርባቸዋል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

  • አለባበሳችንና ውጫዊ ገጽታችን ሊያሳስበን የሚገባው ለምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • ሁላችንም ከአለባበሳችንና ከውጫዊ ገጽታችን ጋር በተያያዘ የየራሳችን ምርጫ ይኖረናል። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች መከተላችን የራሳችንን ምርጫ መተው ሳያስፈልገን ይሖዋን ማስደሰት እንድንችል ይረዳናል። እስቲ ከእነዚህ መሠረታዊ ሥርዓቶች መካከል አንዳንዶቹን እንመልከት።

      1. ከአለባበሳችንና ከውጫዊ ገጽታችን ጋር በተያያዘ ውሳኔ ስናደርግ በየትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ልንመራ ይገባል?

      “በልከኝነትና በማስተዋል፣ ተገቢ [የሆነ] ልብስ” መልበስ ይኖርብናል፤ በተጨማሪም “ለአምላክ ያደርን ነን የሚሉ [ሰዎች] ሊያደርጉት እንደሚገባ” ምንጊዜም ንጽሕናችንን መጠበቅ አለብን። (1 ጢሞቴዎስ 2:9, 10) የሚከተሉትን አራት መሠረታዊ ሥርዓቶች ልብ በል፦ (1) አለባበሳችን “ተገቢ” ሊሆን ይገባል። በጉባኤ ስብሰባዎቻችን ላይ እንዳየኸው የይሖዋ ሕዝቦች በአለባበስና በፀጉር አያያዝ ረገድ የየራሳቸው ምርጫ አላቸው፤ ሆኖም ምርጫቸው የሚያመልኩትን አምላክ እንደሚያከብሩ የሚያሳይ ነው። (2) “በልከኝነት” መልበስ ሲባል የፆታ ስሜትን የሚቀሰቅስ ወይም ወደ ራሳችን ከልክ ያለፈ ትኩረት የሚስብ ልብስ ከመልበስ መቆጠብ ማለት ነው። (3) በየጊዜው የሚመጣውን እያንዳንዱን ፋሽን ባለመከተል ‘አስተዋይ’ እንደሆንን እናሳያለን። (4) ውጫዊ ገጽታችን ‘ለአምላክ ያደርን እንደሆንን’ ማለትም እውነተኛውን አምላክ እንደምናመልክ የሚያሳይ ሊሆን ይገባል።—1 ቆሮንቶስ 10:31

      2. አለባበሳችንን ስንመርጥ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ግምት ውስጥ ማስገባት ያለብን ለምንድን ነው?

      የምንለብሰውን ልብስ የመምረጥ ነፃነት ቢኖረንም የእኛ ምርጫ በሌሎች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ማሰብ አለብን። ማንንም ቅር ላለማሰኘት፣ ከዚህ ይልቅ ‘ባልንጀራችንን የሚጠቅመውንና የሚያንጸውን ነገር በማድረግ ለማስደሰት’ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን።—ሮም 15:1, 2⁠ን አንብብ።

      3. አለባበሳችን ሌሎችን ወደ እውነተኛው አምልኮ ሊስብ የሚችለው እንዴት ነው?

      ሁሌም ሥርዓታማ አለባበስ እንዲኖረን ጥረት ብናደርግም በተለይ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝና በስብከቱ ሥራ ስንካፈል ለአለባበሳችን ልዩ ትኩረት እንሰጣለን። አለባበሳችን ሰዎች በያዝነው አስፈላጊ መልእክት ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ እንቅፋት እንዲሆንባቸው አንፈልግም። ከዚህ ይልቅ ‘የአዳኛችን ትምህርት ውበት እንዲጎናጸፍ’ በማድረግ ሰዎችን ወደ እውነት የሚስብ ሊሆን ይገባል።—ቲቶ 2:10

      ጠለቅ ያለ ጥናት

      ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ አለባበስና ውጫዊ ገጽታ እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

      ሁለት ወንዶች ዳኛ ፊት ቆመው። አንደኛው ሙሉ ልብስ ለብሷል፤ ሌላኛው ደግሞ የተቀዳደደና የተዝረከረከ ልብስ እንዲሁም ኮፍያ አድርጓል

      አለባበሳችን ሥልጣን ላላቸው ሰዎች አክብሮት እንዳለን ወይም እንደሌለን ሊጠቁም ይችላል። ይሖዋ የልባችንን የሚያውቅ ቢሆንም ለእሱ አክብሮት እንዳለን በአለባበሳችንም ማሳየት አለብን

      4. ጥሩ አለባበስ ለይሖዋ አክብሮት እንዳለን ያሳያል

      ለአለባበሳችን ትኩረት የምንሰጥበት ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው? መዝሙር 47:2⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • አለባበሳችን ሰዎች ለይሖዋ ባላቸው አመለካከት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ማወቃችን ምን እንድናደርግ ያነሳሳናል?

      • በስብሰባዎች ላይ ስንገኝና በስብከቱ ሥራ ስንካፈል ለአለባበሳችን ልዩ ትኩረት መስጠታችን አስፈላጊ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      5. ከአለባበስና ከውጫዊ ገጽታ ጋር በተያያዘ ጥሩ ምርጫ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

      ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ “ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር አድርጉ” (10:18)

      ልብሶቻችን ውድ ሆኑም አልሆኑ ንጹሕና ለሁኔታው ተስማሚ መሆን አለባቸው። አንደኛ ቆሮንቶስ 10:24⁠ን እና 1 ጢሞቴዎስ 2:9, 10⁠ን አንብቡ። ከዚያም የሚከተሉትን ዓይነት ልብሶች መልበስ የሌለብን ለምን እንደሆነ ተወያዩ፦

      • የቆሸሸና የተዝረከረከ

      • የተጣበቀ፣ ሰውነትን የሚያሳይ ወይም የፆታ ስሜት የሚቀሰቅስ

      እኛ ክርስቲያኖች በሙሴ ሕግ ሥር ባንሆንም ሕጉ የይሖዋን አመለካከት ለማወቅ ይረዳናል። ዘዳግም 22:5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ወንዶች ሴት የሚያስመስል፣ ሴቶች ደግሞ ወንድ የሚያስመስል ልብስ መልበስ የሌለባቸው ለምንድን ነው?

      አንደኛ ቆሮንቶስ 10:32, 33⁠ን እንዲሁም 1 ዮሐንስ 2:15, 16⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • አለባበሳችን በጉባኤያችን ወይም በአካባቢያችን ያሉ አንዳንድ ሰዎችን ቅር የሚያሰኝ መሆን አለመሆኑን ማሰባችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      • አንተ በምትኖርበት አካባቢ የተለመደው ምን ዓይነት አለባበስ ነው?

      • ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ ለክርስቲያኖች ተገቢ ያልሆኑ ይመስሉሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      በይሖዋ ፊት ተቀባይነት ያላቸው የተለያዩ አለባበሶች አሉ

      በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙና የተለያየ ዘር ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ለክርስቲያኖች ተገቢ የሆነ የተለያየ ልብስ ለብሰው፤ የፀጉር አያያዛቸውም የተለያየ ነው

      አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “የፈለግኩትን ልብስ መልበስ መብቴ ነው።”

      • አንተ በዚህ ሐሳብ ትስማማለህ? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      ማጠቃለያ

      በአለባበስ ረገድ ጥሩ ምርጫ ማድረጋችን ለይሖዋም ሆነ ለሰዎች አክብሮት እንዳለን ያሳያል።

      ክለሳ

      • ይሖዋ በአለባበስ ረገድ ጥሩ ምርጫ እንድናደርግ የሚፈልገው ለምንድን ነው?

      • ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ውሳኔ ስናደርግ በየትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ልንመራ ይገባል?

      • አለባበሳችን ሌሎች ለእውነተኛው አምልኮ ባላቸው አመለካከት ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

      ግብ

      ምርምር አድርግ

      አለባበስህ ለሌሎች ምን መልእክት ያስተላልፋል?

      “አለባበሴ እንዴት ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

      ከመነቀስህ በፊት ቆም ብለህ ማሰብህ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      “መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳት ምን ይላል?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

      ውሳኔ ለማድረግ የሚረዱህ ሌሎች መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው?

      “አለባበሳችሁ አምላክን ያስከብራል?” (መጠበቂያ ግንብ መስከረም 2016)

      አምላክን ማስደሰት ትፈልግ የነበረች አንዲት ሴት ሌሎች በአለባበስ ረገድ ያደረጉትን ምርጫ እንድታከብር የረዳት ምንድን ነው?

      “የሰዎች አለባበስና የፀጉር አያያዝ መሰናክል ሆኖብኝ ነበር” (ንቁ! ላይ የወጣ ርዕስ)

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ