የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ጥር 1
    • የአንባብያን ጥያቄዎች

      ጳውሎስ “ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፣ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ” ሲል ምን ማለቱ ነበር?

      ጳውሎስ የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ በዓል ስለተቋቋመበት መንገድ ሲናገር እንደሚከተለው በማለት ጽፎ ነበር:- “ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፣ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።” (1 ቆሮንቶስ 11:25, 26) አንዳንዶች እዚህ ላይ የተጠቀሰው “ጊዜ ሁሉ” የሚለው ሐረግ የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል በተደጋጋሚ ማለትም ብዙ ጊዜ ሊከበር እንደሚገባው ያሳያል የሚል አመለካከት አላቸው። በመሆኑም የሞቱን መታሰቢያ በዓመት አንድ ጊዜ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ያከብሩታል። ይሁን እንጂ ጳውሎስ እንደዚያ ማለቱ ነበርን?

      ኢየሱስ የሞቱን መታሰቢያ በዓል ካቋቋመ ወደ 2,000 ዓመት ሊሆነው ምንም ያህል አልቀረውም። በመሆኑም የመታሰቢያው በዓል በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንኳን እየተከበረ ከ33 እዘአ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተከብሯል ማለት ነው። ይሁን እንጂ በ1 ቆሮንቶስ 11:​25, 26 ላይ ጳውሎስ እየተናገረ የነበረው የመታሰቢያው በዓል ምን ያህል ጊዜ መከበር እንዳለበት ሳይሆን እንዴት መከበር እንዳለበት ነው። ጳውሎስ እዚህ ጥቅስ ላይ የተጠቀመበት የግሪክኛ ቃል “ብዙ ጊዜ” ወይም “በተደጋጋሚ” የሚል ትርጉም ያለውን ፖላኪስ ሳይሆን “እንደዚህ ባደረጋችሁ ቁጥር” የሚል ትርጓሜ ያለውን ኦሳኪስ የሚለውን ቃል ነው። ጳውሎስ ‘እንደዚህ ባደረጋችሁ ቁጥር የጌታን ሞት ትናገራላችሁ’ ማለቱ ነበር።a

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ጥር 1
    • a በ1 ሳሙኤል 1:​3, 7 አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ የሚገኘውን ዘገባ ተመልከት። እዚህ ላይ “ጊዜ ሁሉ” የሚለው አገላለጽ ሕልቃናና ሁለት ሚስቶቹ “በየዓመቱ” ወይም በዓመት አንድ ጊዜ ሴሎ ወደሚገኘው የመገናኛ ድንኳን ሲሄዱ የተፈጸመውን ሁኔታ ያመለክታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ