የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መንፈሳዊ ሰው መሆን—ምን ማለት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | የካቲት
    • መንፈሳዊ ሰው በምን ተለይቶ ይታወቃል?

      3. መጽሐፍ ቅዱስ በዓለማዊ ሰው እና በመንፈሳዊ ሰው መካከል ምን ልዩነት እንዳለ ይገልጻል?

      3 ሐዋርያው ጳውሎስ ‘መንፈሳዊ ሰውን’ እና ‘ዓለማዊ ሰውን’ በማነጻጸር ያሰፈረው ሐሳብ መንፈሳዊ ሰው መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። (1 ቆሮንቶስ 2:14-16⁠ን አንብብ።) ‘በመንፈሳዊ ሰው’ እና ‘በዓለማዊ ሰው’ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ጳውሎስ እንደገለጸው “ዓለማዊ ሰው . . . ከአምላክ መንፈስ የሆኑትን ነገሮች አይቀበልም።” ምክንያቱም “እንዲህ ያሉት ነገሮች ለእሱ ሞኝነት ናቸው”፤ ደግሞም “ሊረዳቸው አይችልም።” በሌላ በኩል ግን “መንፈሳዊ ሰው ሁሉንም ነገር ይመረምራል” እንዲሁም “የክርስቶስ አስተሳሰብ” አለው። ጳውሎስ መንፈሳዊ ሰዎች እንድንሆን አበረታቶናል። ዓለማዊ ሰውን ከመንፈሳዊ ሰው ለመለየት የሚያስችሉን ሌሎች ነገሮችስ የትኞቹ ናቸው?

  • መንፈሳዊ ሰው መሆን—ምን ማለት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | የካቲት
    • 6. መንፈሳዊ ሰው ተለይቶ የሚታወቅባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

      6 “መንፈሳዊ ሰው” መሆን ሲባልስ ምን ማለት ነው? ከዓለማዊ ሰው በተለየ መልኩ መንፈሳዊ ሰው ከአምላክ ጋር ላለው ዝምድና ትልቅ ቦታ ይሰጣል። መንፈሳዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ‘አምላክን ለመምሰል’ ጥረት ያደርጋሉ። (ኤፌ. 5:1) ይህም ሲባል የይሖዋን አስተሳሰብ ለመረዳት ብሎም ነገሮችን እሱ በሚመለከትበት መንገድ ለመመልከት ይጥራሉ ማለት ነው። ለእነዚህ ሰዎች አምላክ እውን ሆኖ ይታያቸዋል። ሥጋዊ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች በተቃራኒ መንፈሳዊ የሆኑ ሰዎች፣ መላ ሕይወታቸውን ከይሖዋ መሥፈርቶች ጋር በሚስማማ መንገድ ለመምራት የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። (መዝ. 119:33፤ 143:10) መንፈሳዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው በሥጋ ሥራዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ “የመንፈስ ፍሬ” ለማፍራት ጥረት ያደርጋል። (ገላ. 5:22, 23) ነጥቡን ግልጽ ለማድረግ፦ ነገሮችን ሁልጊዜ በአዎንታዊ መንገድ የሚመለከት ሰው አዎንታዊ አስተሳሰብ አለው ይባላል፤ በተመሳሳይም ለመንፈሳዊ ነገሮች ትልቅ ቦታ የሚሰጥ ሰው መንፈሳዊ አስተሳሰብ አለው ሊባል ይችላል።

      7. መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳዊ አስተሳሰብ መያዝን በተመለከተ ምን ይላል?

      7 መንፈሳዊ አስተሳሰብ መያዝን የሚያበረታቱ ሐሳቦችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። ለምሳሌ ማቴዎስ 5:3 “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ነውና” ይላል። ሮም 8:6 ደግሞ መንፈሳዊ አስተሳሰብ ማዳበር ያለውን ጥቅም ሲገልጽ “በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሞት ያስከትላልና፤ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ግን ሕይወትና ሰላም ያስገኛል” ይላል። በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ካደረግን በአሁኑ ጊዜ ከአምላክ ጋር ያለንን ሰላም ጠብቀን መኖርና ውስጣዊ ሰላም ማግኘት እንችላለን፤ ወደፊት ደግሞ የዘላለም ሕይወት እናገኛለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ