የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የፍቅር መንገድ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 15
    • 4. መጽሐፍ ቅዱስ ቅናትን በተመለከተ ምን ማስተዋል ይሰጠናል?

      4 ጳውሎስ ፍቅርን በተመለከተ የመግቢያ ሐሳብ ካቀረበ በኋላ “ፍቅር አይቀናም” ሲል ለቆሮንቶስ ሰዎች ጽፏል። (1 ቆሮንቶስ 13:​4) ቅናት ሌሎች ባገኙት ብልጽግና ወይም ስኬት ቅር በመሰኘት ሊገለጽ ይችላል። ይህ ዓይነቱ ቅናት አካልን፣ ስሜትንና መንፈስን ይጎዳል።​—⁠ምሳሌ 14:​30፤ ሮሜ 13:​13፤ ያዕቆብ 3:​14-16

      5. በአንዳንድ ቲኦክራሲያዊ መብቶች ረገድ ቸል እንደተባልን ሆኖ ሲሰማን የሚያድርብንን የቅናት ስሜት ለማሸነፍ ፍቅር እንዴት ሊረዳን ይችላል?

      5 ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ:- ‘በአንዳንድ ቲኦክራሲያዊ መብቶች ረገድ ቸል እንደተባልኩ ሆኖ ሲሰማኝ ቅናት ያድርብኛልን?’ መልስህ አዎን፣ ከሆነ ተስፋ አትቁረጥ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ያዕቆብ ‘የቅናት ዝንባሌ’ ፍጽምና በሌላቸው ሰዎች ሁሉ ውስጥ ያለ ነገር መሆኑን እንድናስታውስ ያደርገናል። (ያዕቆብ 4:​5) ለወንድምህ ያለህ ፍቅር ሚዛንህን እንድትጠብቅ ሊረዳህ ይችላል። አንድ ሰው በረከት በሚያገኝበት ወይም በሚመሰገንበት ጊዜ አንተ እንድትቀየም ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር እንደሆነ አድርገህ ከመመልከት ይልቅ ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ እንዲልህ ፍቅር ሊረዳህ ይችላል።​—⁠ከ1 ሳሙኤል 18:​7-9 ጋር አወዳድር።

      6. በመጀመሪያው መቶ ዘመን በነበረው የቆሮንቶስ ጉባኤ ውስጥ ምን አስቸጋሪ ሁኔታ ተከስቶ ነበር?

      6 ጳውሎስ ፍቅር “አይመካም፣ አይታበይም” በማለት አክሎ ተናግሯል። (1 ቆሮንቶስ 13:​4) አንድ ዓይነት ተሰጥዎ ወይም ችሎታ ካለን በሌሎች ዘንድ ጉራ መንዛት የለብንም። ከሁኔታው ለመረዳት እንደሚቻለው ወደ ጥንቱ የቆሮንቶስ ጉባኤ ሾልከው የገቡ አንዳንድ ትዕቢተኛ ሰዎች እንዲህ ያለ ችግር ነበራቸው። ምናልባት ሐሳቦችን የማብራራት ወይም ነገሮችን በጥሩ ሁኔታ የማከናወን የላቀ ችሎታ ይኖራቸው ይሆናል። በጉባኤው መካከል መከፋፈል እንዲኖር አስተዋጽኦ ያደረገው የሌሎችን ትኩረት ወደ ራሳቸው ለመሳብ ያደረጉት ጥረት ሳይሆን አይቀርም። (1 ቆሮንቶስ 3:​3, 4፤ 2 ቆሮንቶስ 12:​20) ይህ ጉዳይ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ስለነበር ‘ዋነኞቹ ሐዋርያት’ በማለት የተቻቸውን ‘ሞኞች በመታገሣቸው’ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን መውቀስ ግድ ሆኖበታል።​—⁠2 ቆሮንቶስ 11:​5, 19, 20

      7, 8. ያለንን ተሰጥዎ አንድነትን ለማጎልበት እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል ከመጽሐፍ ቅዱስ አስረዳ።

      7 ዛሬም ተመሳሳይ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል። ለምሳሌ አንዳንዶች በአገልግሎት ስላገኙት ስኬት ወይም በአምላክ ድርጅት ውስጥ ስላሏቸው መብቶች በጉራ የመናገር አዝማሚያ ሊታይባቸው ይችላል። በጉባኤ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ሰዎች የሌላቸው የተለየ ተሰጥኦ ወይም ችሎታ ቢኖረን እንኳ ትዕቢት እንዲያድርብን ምክንያት ይሆነናልን? ከዚህ ይልቅ ያለንን ማንኛውንም ዓይነት ተፈጥሯዊ ችሎታ ራሳችንን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሳይሆን አንድነትን ለማጎልበት ልንጠቀምበት ይገባል።​—⁠ማቴዎስ 23:​12፤ 1 ጴጥሮስ 5:​6

      8 ጳውሎስ አንድ ጉባኤ ብዙ ብልቶች ቢኖሩትም ‘አካሉን ያገጣጠመው አምላክ’ እንደሆነ ጽፏል። (1 ቆሮንቶስ 12:​19-26) “አገጣጠመ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ቀለም በሚቀላቀልበት ጊዜ እንደሚዋሃደው እርስ በርስ ስምም ሆኖ መዋሃድን ያመለክታል። ስለዚህ በጉባኤው ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ስለ ችሎታዎቹ ጉራውን መንዛትና ሌሎችን ለመጫን መሞከር የለበትም። ኩራትና የሥልጣን ጥማት በአምላክ ድርጅት ውስጥ ቦታ የላቸውም።​—⁠ምሳሌ 16:​19፤ 1 ቆሮንቶስ 14:​12፤ 1 ጴጥሮስ 5:​2, 3

  • የፍቅር መንገድ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 15
    • 11. (ሀ) በደግነት ላይ የተመሠረተና ተገቢ የሆነ ፍቅር ማሳየት የምንችለው በምን መንገዶች ነው? (ለ) ክፉ በሆነ ነገር እንደማንደሰት እንዴት ልናሳይ እንችላለን?

      11 በተጨማሪም ጳውሎስ ፍቅር “ደግ” እንደሆነና “ሥርዓተ ቢስ” እንዳልሆነ ጽፏል። (1 ቆሮንቶስ 13:​4, 5 የ1980 ትርጉም) አዎን፣ ፍቅር ስድ፣ ባለጌ ወይም ግብረገብነት የጎደለን እንድንሆን አይፈቅድልንም። ከዚህ ይልቅ ስለ ሌሎች ስሜት እናስባለን። ለምሳሌ ያህል አፍቃሪ የሆነ ሰው የሌሎችን ሕሊና የሚረብሹ ነገሮችን ከማድረግ ይቆጠባል። (ከ1 ቆሮንቶስ 8:​13 ጋር አወዳድር።) ፍቅር “ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም።” (1 ቆሮንቶስ 13:​6) የይሖዋን ሕግ የምንወድ ከሆነ የብልግና ድርጊቶችን በግዴለሽነት አንመለከትም ወይም አምላክ በሚጠላቸው ነገሮች አንዝናናም። (መዝሙር 119:​97) ፍቅር በሚያፈርሱ ሳይሆን በሚያንጹ ነገሮች እንድንደሰት ይረዳናል።​—⁠ሮሜ 15:​2፤ 1 ቆሮንቶስ 10:​23, 24፤ 14:​26

  • የፍቅር መንገድ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | የካቲት 15
    • 16. ፍቅር ታጋሾች እንድንሆን ሊረዳን የሚችለው በየትኞቹ ሁኔታዎች ሥር ነው?

      16 ጳውሎስ በመቀጠል “ፍቅር ይታገሣል” ይለናል። (1 ቆሮንቶስ 13:​4) አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎችን ምናልባትም ለረዥም ጊዜ ችለን እንድንጸና ሊያደርገን ይችላል። ለምሳሌ ያህል ብዙ ክርስቲያኖች በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ ለዓመታት ኖረዋል። ሌሎች ደግሞ “በጌታ” የሆነ ተስማሚ የትዳር ጓደኛ ባለማግኘታቸው ሳይወዱ ነጠላ ሆነዋል። (1 ቆሮንቶስ 7:​39፤ 2 ቆሮንቶስ 6:​14) ሌሎቹ ደግሞ ከማይድን በሽታ ጋር እየታገሉ ለመኖር ይገደዳሉ። (ገላትያ 4:​13, 14፤ ፊልጵስዩስ 2:​25-30) በዚህ ፍጽምና በጎደለው ዓለም ውስጥ በዚህም ሆነ በዚያ ጽናት የማይጠይቅ ሕይወት የሚመራ ሰው እንደሌለ የተረጋገጠ ነው።​—⁠ማቴዎስ 10:​22፤ ያዕቆብ 1:​12

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ