የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ፈጽሞ የማይከስመውን ፍቅርን አዳብሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ታኅሣሥ 15
    • 13. (ሀ) የ2010 የዓመት ጥቅስ ምንድን ነው? (ለ) ፍቅር ፈጽሞ የማይከስመው እንዴት ነው?

      13 ጳውሎስ በመቀጠል ፍቅር የሚያደርገውንና የማያደርገውን ነገር ገልጿል። (1 ቆሮንቶስ 13:4-8⁠ን አንብብ።) እስቲ ትንሽ ቆም በልና ፍቅር ከሚጠይቃቸው ብቃቶች አንጻር ራስህን መርምር። በዋነኝነት በቁጥር 7 መጨረሻ ላይና በቁጥር 8 መጀመሪያ ላይ በሚገኘው ‘ፍቅር ሁሉን ነገር በጽናት ይቋቋማል። ፍቅር ፈጽሞ አይከስምም’ በሚለው የ2010 የዓመት ጥቅስ ላይ ትኩረት አድርግ። ጳውሎስ በቁጥር 8 ላይ መተንበይንና በልሳን መናገርን ጨምሮ የክርስቲያን ጉባኤ ጨቅላ እያለ ተሰጥተው የነበሩ የመንፈስ ስጦታዎች ሁሉ የሚያበቁበት ወይም የሚቀሩበት ጊዜ እንደሚመጣ ተናግሯል። ፍቅር ግን ምንጊዜም ይኖራል። የይሖዋ ዋነኛ ባሕርይ ፍቅር ነው፤ ይሖዋ ደግሞ ዘላለማዊ ነው። በመሆኑም ፍቅር ፈጽሞ አይከስምም ወይም መጨረሻ የለውም። ፍቅር ዘላለማዊ የሆነው አምላካችን ባሕርይ ሆኖ ለዘላለም ይቀጥላል።—1 ዮሐ. 4:8

  • ፈጽሞ የማይከስመውን ፍቅርን አዳብሩ
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ታኅሣሥ 15
    • ፍቅር ፈጽሞ አይከስምም

      20, 21. (ሀ) ፍቅር ከሁሉ ነገር ይበልጣል የምንለው ለምንድን ነው? (ለ) የፍቅርን መንገድ ለመከታተል ቁርጥ ውሳኔ ያደረግከው ለምንድን ነው?

      20 ከሁሉ የላቀውን የፍቅር መንገድ መከታተል የጥበብ እርምጃ መሆኑን በዛሬው ጊዜ ከሚገኙ የይሖዋ ሕዝቦች መረዳት እንችላለን። በእርግጥም ፍቅር ከማንኛውም ነገር ይበልጣል። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን እውነታ ጎላ አድርጎ የገለጸው እንዴት እንደሆነ ልብ በል። በመጀመሪያ የመንፈስ ስጦታዎች እንደሚቀሩ እንዲሁም ጨቅላ የነበረው የክርስቲያን ጉባኤ ወደ ጉልምስና ደረጃ እንደሚደርስ ገልጿል። ከዚያም “ይሁን እንጂ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እነዚህ ሦስቱ እንዳሉ ይቀጥላሉ፤ ከእነዚህ መካከል የሚበልጠው ግን ፍቅር ነው” በማለት ደምድሟል።—1 ቆሮ. 13:13

      21 ወደፊት እምነት ያደረግንባቸው ነገሮች እውን ይሆናሉ፤ ከዚያ በኋላ በእነዚያ ነገሮች ላይ እምነት ማሳደር አስፈላጊ አይሆንም። ሁሉም ነገር አዲስ ሲሆን፣ ለማየት እንናፍቃቸው የነበሩ ተስፋዎች ስለሚፈጸሙ ከዚያ በኋላ በእነዚያ ነገሮች ላይ ተስፋ ማድረግ አያስፈልገንም። ስለ ፍቅርስ ምን ማለት ይቻላል? ፍቅር ፈጽሞ አይከስምም ወይም መጨረሻ የለውም፤ እንዲያውም ለዘላለም ይኖራል። እኛም ለዘላለም ስለምንኖር የአምላክን ፍቅር የተለያዩ ገጽታዎች ይበልጥ እንደምናይና እንደምንረዳ ምንም ጥርጥር የለውም። አንተም ፈጽሞ የማይከስመውንና ከሁሉ የላቀውን የፍቅር መንገድ በመከታተል የአምላክን ፈቃድ የምትፈጽም ከሆነ ለዘላለም መኖር ትችላለህ።—1 ዮሐ. 2:17

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ