የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የኢየሱስ ትንሣኤ በእርግጥ ተፈጽሟል?
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | መጋቢት 1
    • [በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      ጳውሎስ፣ ክርስቲያኖች ስለ ትንሣኤ ያላቸው እምነት በውሸት ላይ የተመሠረተ ነው የሚል አመለካከት አልነበረውም። ኢየሱስ ከሞት እንደተነሣ ያውቅ ስለነበረ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ማስረጃዎቹን ጠቅለል አድርጎ ሲያስቀምጥላቸው እንዲህ አላቸው፦ “ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረም፤ ደግሞም ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉት በሦስተኛው ቀን ተነሳ፤ ለኬፋም ታየ፤ ከዚያም ለአሥራ ሁለቱ ታየ።”b አክሎም እንዲህ አለ፦ “በኋላ ደግሞ በአንድ ጊዜ ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ወንድሞች የታየ ሲሆን አብዛኞቹ እስካሁን በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን በሞት አንቀላፍተዋል። ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ በሙሉ ታየ፤ በመጨረሻ ደግሞ . . . ለእኔ ተገለጠልኝ።”—1 ቆሮንቶስ 15:3-8

  • የኢየሱስ ትንሣኤ በእርግጥ ተፈጽሟል?
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | መጋቢት 1
    • b የአስቆሮቱ ይሁዳ ከሞተ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የሐዋርያቱ ቁጥር 11 የነበረ ቢሆንም “አሥራ ሁለቱ” የሚለው አገላለጽ ያሉትን ሐዋርያት ለማመልከትም ተሠርቶበታል። በአንድ ወቅት ኢየሱስ፣ ቶማስ በሌለበት ለሐዋርያቱ በተገለጠላቸው ጊዜ ቁጥራቸው 10 ብቻ ቢሆንም 12ቱ ተብለዋል።—ዮሐንስ 20:24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ