-
ከኢየሱስ ታናሽ ወንድም ተማሩመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ጥር
-
-
እንደ ያዕቆብ ምንጊዜም ትሑት ሁኑ
ያዕቆብ ኢየሱስ ከተገለጠለት በኋላ በትሕትና እርምጃ ወስዷል፤ ከዚያ ጊዜ አንስቶ ታማኝ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ አገልግሏል (ከአንቀጽ 5-7ን ተመልከት)
5. ያዕቆብ፣ ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ሲገለጥለት ምን ምላሽ ሰጠ?
5 ያዕቆብ የኢየሱስ ታማኝ ተከታይ የሆነው መቼ ነው? ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ “ለያዕቆብ ታየ፤ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ በሙሉ ታየ።” (1 ቆሮ. 15:7) ያዕቆብ ከኢየሱስ ጋር የተገናኘበት ይህ አጋጣሚ በሕይወቱ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። በኋላ ላይ ሐዋርያቱ ኢየሩሳሌም ባለ አንድ ደርብ ላይ ሆነው ቃል የተገባላቸውን መንፈስ ቅዱስ ይጠባበቁ በነበረበት ወቅት ያዕቆብ አብሯቸው ነበር። (ሥራ 1:13, 14) ከጊዜ በኋላ ያዕቆብ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው የበላይ አካል አባል ሆኖ የማገልገል መብት አግኝቷል። (ሥራ 15:6, 13-22፤ ገላ. 2:9) ከ62 ዓ.ም. ገደማ በፊት ደግሞ በመንፈስ መሪነት ለቅቡዓን ክርስቲያኖች ደብዳቤ ጽፏል። ተስፋችን ሰማያዊም ይሁን ምድራዊ ይህ ደብዳቤ በዛሬው ጊዜ ያለነውን ሁሉ ይጠቅመናል። (ያዕ. 1:1) በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖረው ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ እንደዘገበው ያዕቆብ የአይሁድ ሊቀ ካህናት የሆነው ሐናንያ (የሐና ልጅ) ባስተላለፈው ትእዛዝ ተገድሏል። ያዕቆብ ምድራዊ ሕይወቱን እስካጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ ይሖዋን በታማኝነት አገልግሏል።
-