-
የኢየሱስ ትንሣኤ በእርግጥ ተፈጽሟል?መጠበቂያ ግንብ—2013 | መጋቢት 1
-
-
በጥንቷ ቆሮንቶስ የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች የትንሣኤ ጉዳይ ግራ አጋብቷቸው የነበረ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ትንሣኤ ቃል በቃል የሚፈጸም ነገር እንደሆነ ጭራሹኑ አያምኑም ነበር። ሐዋርያው በዚያ ለነበሩ ክርስቲያኖች በጻፈላቸው የመጀመሪያ ደብዳቤ ላይ፣ ትንሣኤ ውሸት ከሆነ ምን ውጤት ሊከተል እንደሚችል ዘርዝሯል። እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “የሙታን ትንሣኤ ከሌለማ ክርስቶስም አልተነሳም ማለት ነዋ! ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ ስብከታችን ከንቱ ነው፤ እምነታችንም ከንቱ ነው። ከዚህም በተጨማሪ . . . ሐሰተኞች የአምላክ ምሥክሮች ሆነን ተገኝተናል ማለት ነው። . . . [ደግሞም] እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ አሁንም ገና ከነኃጢአታችሁ ናችሁ ማለት ነው። . . . የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሆነው በሞት ያንቀላፉትም ጠፍተዋል ማለት ነው።”—1 ቆሮንቶስ 15:13-18
“በአንድ ጊዜ ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ወንድሞች የታየ ሲሆን . . . ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ በሙሉ ታየ፤ በመጨረሻ ደግሞ . . . ለእኔ ተገለጠልኝ።”—1 ቆሮንቶስ 15:6-8
-
-
የኢየሱስ ትንሣኤ በእርግጥ ተፈጽሟል?መጠበቂያ ግንብ—2013 | መጋቢት 1
-
-
ክርስቶስ ከሞት አልተነሳም ብሎ ማመን የሚያስከትለው ውጤት በዚህ ብቻ አያበቃም። ክርስቶስ ከሞት ካልተነሳ የክርስትና እምነት ከንቱ፣ ባዶና ውሸት ይሆን ነበር። በተጨማሪም ጳውሎስና ሌሎች ደቀ መዛሙርት እየዋሹ ያሉት ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስን አስነስቶታል ብለው ስለሚናገሩለት ስለ ይሖዋ አምላክም ጭምር ይሆን ነበር። ከዚህም በላይ “ክርስቶስ ስለ ለኃጢአታችን ሞተ” የሚለው አባባልም ሐሰት ይሆን ነበር፤ ምክንያቱም አዳኙ ራሱ ከሞት ካልዳነ ሌሎችን ሊያድን አይችልም። (1 ቆሮንቶስ 15:3) ይህ ደግሞ፣ በተለያየ ምክንያት የሞቱና አንዳንዶቹም ሰማዕታት እስከመሆን የደረሱ ክርስቲያኖች ትንሣኤ እናገኛለን በሚል ከንቱ ተስፋ ጠፍተው ቀርተዋል ማለት ይሆን ነበር።
-