የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ሞት ይሻራል”
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ሐምሌ 1
    • 10 “ፍጻሜ” የተባለው የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ፍጻሜ ሲሆን በዚያን ጊዜም ኢየሱስ በትሕትናና በታማኝነት መንግሥቱን ለአምላኩና ለአባቱ ያስረክባል። (ራእይ 20:​4) በዚያን ጊዜ አምላክ የነበረው ‘ሁሉን በክርስቶስ የመጠቅለል’ ዓላማ ፍጻሜውን ያገኛል። (ኤፌሶን 1:​9, 10) አስቀድሞ ግን ክርስቶስ የአምላክን ሉዓላዊ ፈቃድ የሚቃወመውን ‘አለቅነት ሁሉ፣ ሥልጣን ሁሉና ኃይል’ ያጠፋል። ይህ በአርማጌዶን ከሚመጣው ጥፋት የበለጠ ነገርን ያካትታል። (ራእይ 16:​16፤ 19:​11-21) ጳውሎስ “[ክርስቶስ] ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው” ብሏል። (1 ቆሮንቶስ 15:​25, 26) አዎን፣ የአዳማዊ ኃጢአትና ሞት ርዝራዥ ተጠራርጎ ይጠፋል። ከዚያም አምላክ ሙታንን ወደ ሕይወት መልሶ በማምጣት ‘የመታሰቢያ መቃብሮችን’ ባዶ ያደርጋል።​—⁠ዮሐንስ 5:​28 NW

  • “ሞት ይሻራል”
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ሐምሌ 1
    • 15. ዳግመኛ ሕያው የሚሆኑት ሰዎች ‘በመጻሕፍት ተጽፎ እንደነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድ ይቀበላሉ’ ሲባል ምን ማለት ነው?

      15 እነዚህ ዳግመኛ ሕያው የሚሆኑ ሰዎች ‘በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድ የሚቀበሉት’ እንዴት ነው? እነዚህ መጻሕፍት ቀደም ሲል የሠሯቸውን ሥራዎች ዘግበው የያዙ አይደሉም፤ በሞቱበት ጊዜ በሕይወት ዘመናቸው ከፈጸሟቸው ኃጢአቶች ነፃ ወጥተዋል። (ሮሜ 6:​7,23) ይሁን እንጂ ከሞት ከተነሡም በኋላ ቢሆን በአዳማዊ ኃጢአት ሥር ይሆናሉ። እንግዲያው እነዚህ መጻሕፍት ከኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚዎች ለመሆን እንዲችሉ ሊከተሏቸው የሚገቡትን መለኮታዊ መመሪያዎች የያዙ መሆን አለባቸው። የአዳማዊ ኃጢአት የመጨረሻ ርዝራዥ ከተወገደ በኋላ ‘ሞት ሙሉ በሙሉ ይሻራል።’ በሺህ ዓመቱ ማብቂያ ላይ አምላክ ‘ሁሉ በሁሉ ይሆናል።’ (1 ቆሮንቶስ 15:​28) ከዚያ በኋላ ሰው ሊቀ ካህናት ወይም ቤዛ አያስፈልገውም። ሁሉም የሰው ዘር አዳም በመጀመሪያ ወደ ነበረው የፍጽምና ደረጃ ይደርሳል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ